Daily Weather Report 26 March 15

Weather Summary for previous day

March 14, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት አካባቢዎች እንዲሁም በምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በይርጋጨፌ፣ ብላቴ፣ ሀዋሳ፣ ጂንካ፣ ዲላ፣ አርባምንጭ፣ ምዕራብ አባያ፣ ቴፒ፣ ጉበቲ፣ ቦሬ፣ ቡሌሆራ፣ ጋቲራ፣ ሊሙገነት፣ አጋሮ፣ ነቀምቴ፣ ባቱ፣ መካነሰላም፣ ነፋስመውጫ እና ላሊበላ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38.4-41.6 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover in the areas that benefited from the Belg rain, as well as in the western parts of the country. In this regard, light to moderate (1-29 mm) rainfall was recorded in Yirgacheffe, Bilatte, Hawassa, Jinka, Dilla, Arba Minch, Morab Abaya, Tepi, Gubeti, Bore, Bulehora, Gatira, Limuganet, Agaro, Nekemte, Batu, Meknesalam, Nefasmewicha, and Lalibela. On the other hand, in Gambella, Fugnido, and Gode, the maximum temperature of the day was recorded as 38.4-41.6 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

March 16, 2026

በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች እንዲሁም በሰሜን ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ቤንችሸኮ፣ ኮንታ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ እና ከአማራ ክልል የሰሜንና ምስራቅ ጎጃም እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ሸርኮሌ፣ ማንኩሽ፣ ኩምሩክ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ ሰመራ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

Tomorrow, there will be cloud cover in the areas of our country that will benefit from the Belg rains, as well as in the northwest and western parts of the country. In this regard, from Oromia region, Guji and West Guji, Borena, Jimma, Ilubabor, Kelem, and West Wellega zones; from the southern Ethiopian region the zones of Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, and South Omo; Sidama region zones, from the southwest Ethiopia region Sheka, Kefa, Benchsheko, Konta, and West Omo zones; from the Gambella region, the zones of Agnuwak, Itang, and Majang; and in the Amhara region the north and East Gojjam and South Gondar zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. On the other hand, in Metema, Sherkole, Mankush, Kurmuk, Gambella, Fugnido, Abobo, Awash Arba, Gewane, Elidar, Semara, Gode, and Kebridehar, the maximum temperature of the day will reach 35-40 degrees Celsius.