Daily Weather Report 26 March 14

Weather Summary for previous day

March 13, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚህም ጋር በዲላ፣ ኮንሶ፣ ጂንካ፣ አርባምንጭ፣ ወላይታሶዶ፣ አማን፣ ቦሬ፣ ጭራ፣ በደሌ፣ ነቀምቴ፣ ወገልጤና፣ መካነሰላም እና ደብረማርቆስ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ37.4-42.5 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was a cloud cover over the areas of the country that benefited from the Belg season. In this regard, light to moderate rainfall (1-29 mm) was recorded in Dilla, Konso, Jinka, Arba Minch, Wolaitasodo, Aman, Bore, Chira, Bedele, Nekemte, Wegeltena, Mekaneselam, and Debre Markos. On the other hand, in Gambella, Fugnido, Kebridehar, and Gode, the daily maximum temperature was recorded at 37.4-42.5 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

March 15, 2026

በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት አካባቢዎች እንዲሁም በሰሜን ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምስራቅ ወለጋ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ቤንችሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች እና ከአማራ ክልል የምስራቅ ጎጃም፣ ደቡብ ወሎ፣ ማዕካለዊ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ሸርኮሌ፣ ኩምሩክ፣ በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ።

Tomorrow, there will be cloud cover and accumulation in the areas benefiting from the Belg season as well as in the northwest and western parts of the country. In this regard the Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, South Omo, and Konso zones of the Southern Ethiopian region; the West Arsi, Guji, West Guji, Borena, Jimma, Ilubabor, East Wellga, and West Shewa zones from the Oromia region; the Yem Special Zone, Hadia, Halaba, Kembata, and Tembaro zones from the Central Ethiopian region; Sheka, Kefa, Benchsheko, Dauro, West Omo and Konta zones from the Southwest region of Ethiopia; from Gambella region Agnewak, Itang, and Majang zones; and East Gojjam, South Wollo, Central, and South Gondar zones in the Amhara region will receive light to moderate rainfall (1-29 mm). Therefore, the amount and distribution of rainfall will be of great importance for Belg agricultural activities. On the other hand, in Metema, Sherkole, Kurmuk, Gambella, Fugnido, Abobo, Gode, and Kebridehar, the daily maximum temperature will expected to 35-40 degrees Celsius.