Daily Weather Report 26 March 13
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ በአርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ጅማ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ሐዋሳ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜን ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ትግራይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ የነበራቸው ሲሆን፤ በጎብዬ እና ሐይቅ ከባድ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ መንደር 11፣ የጭላ፣ ማይሃንሳ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-41.2°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday the areas of the country that benefited from the belg rains had cloud cover. In addition, light to moderate rainfall was recorded in Borena, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Jimma, West, Southwest and East Shewa, Hawassa, Gamo, Gofa, South Omo, East Gojam, Waghemra, North Wollo, North Shewa, South and East Tigray; heavy rainfall was recorded in Gobye and Lake. On the other hand, the maximum temperature of the day was recorded at 35-41.2°C in Gambella, Village 11, Yecla, Mayhansa, Semera, Elidar, Gewane, Awash Arba, Kebridehar and Gode.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች ላይ የተስፋፋ የደመና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ፤ ባሌ፣ ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ እና ኮንታ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው መካከለኛ መጠን (ከ11-29ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ የሚያገኙ ሲሆንና፤ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ደግሞ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከኦሮሚያ ክልል የደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ሸዋ እና ጅማ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከአማራ ክልል የሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ ዞን ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል። በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠን እና ስርጭት የበልግ የግብርና ስራዎችን ለማከናወን እና ለአርብቶ አደር አካባቢዎችም ለእንስሳት መኖና ለመጠጥ ውሀ አቅርቦትን ለማሻሻል ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል። በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ መተማ፣ ቋራ፣ ሁመራ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 38 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ ፡፡
Tomorrow there will be widespread cloud cover over the areas benefiting from the belg rains. In addition, the Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones of the Southern Ethiopian Region; the Guji and West Guji, Borena and East Borena zones of the Oromia Region; the Bale, West Arsi zones; all zones of the Sidama Region; the Gurage, East Gurage, Marekko Special Zone, Yem Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zones of the Central Ethiopian Region; the Bench Sheko, Sheka, Kefa and Konta zones of the Southwestern Ethiopian Region will receive moderate rainfall (11-29 mm) in many places; and in a few places, heavy rainfall of more than 30 mm will be experienced. In addition, there will be light rain in the South West, West, North Shewa and Jimma zones of Oromia region; Addis Ababa; North and South Gondar, Waghema, North and South Wollo and East Gojam zones of Amhara region and the Central zone of Tigray region. Therefore, the amount and distribution of rainfall will be of great importance for carrying out belg agricultural activities and improving the supply of fodder and drinking water for pastoral areas. On the other hand, the maximum temperature of the day in Gambella, Fugendo, Asosa, Metekel, Metema, Quara, Humera and Gode will be recorded as 35 to 38 degrees Celsius.