Daily Weather Report 26 March 12

Weather Summary for previous day

March 11, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ጅማ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ሐዋሳ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜን ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ የነበራቸው ሲሆን፤ በቡልቂ ከባድ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ላሬ፣ መንደር 11፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-38.4°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday the areas of the country that benefited from the belg rains had cloud cover. In addition, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Jimma, West, Southwest and East Shewa, Hawassa, Wolaita, Gamo, Gofa, South Omo, East Gojam, Waghemra, North Wollo, North Shewa, Central, South and Southeast Tigray experienced light to moderate rainfall; while heavy rainfall was recorded in Bulki. On the other hand, Gambella, Lare, Village 11, Semera, Elidar, Gewane, Awash Arba, Kebridehar and Gode recorded the highest temperature of the day at 35-38.4°C.

Weather Forecast for next day

March 13, 2026

በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ፤ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ እና ኮንታ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው መካከለኛ መጠን (ከ11-29ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ የሚያገኙ ሲሆን፣ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ደግሞ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከኦሮሚያ ክልል የደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ሸዋ እና ጅማ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከአማራ ክልል የሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ደቡብ ዞኖች እና ከአፋር ክልል የቅልበቲ ዞን ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል። በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠን እና ስርጭት የበልግ የግብርና ስራዎችን ለማከናወን እና ለአርብቶ አደር አካባቢዎችም ለእንስሳት መኖና ለመጠጥ ውሀ አቅርቦትን ለማሻሻል ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል። በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ አቦቦ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ መተማ፣ ቋራ፣ ሠመራ፣ ጎዴ እና ዶሎኦዶ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover in the belg main and second rainy seasons of our country. In addition, in the Southern Ethiopian Region, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; in the Oromia Region, Guji and West Guji, Borena and East Borena; Bale, Arsi and West Arsi, West and East Hararge zones; in all Sidama Region zones; in the Central Ethiopian Region, Gurage, East Gurage, Marekko Special Zone, Silte, M' Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zones; The Bench Sheko, Sheka, Kefa and Konta zones of the Southwestern Ethiopian region will receive moderate rainfall (11-29 mm) in most areas, with heavy rainfall in a few areas. In addition, the South West, West, North Shewa and Jimma zones of Oromia region; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; North and South Gondar, Waghema, North and South Wollo, North Shewa, Oromo National Special Zone and East Gojam zones of Amhara region; Central, East, South East and South zones of Tigray region and Kelbeti zone of Afar region will have light rain. Therefore, the amount and distribution of rainfall will be of great importance for carrying out belg agricultural activities and improving the supply of fodder and drinking water for pastoral areas. On the other hand, the maximum temperature of the day in Gambella, Abobo, Asosa, Metekel, Metema, Quara, Samara, Gode and Doloodo will be recorded as 35 to 40 degrees Celsius.