Daily Weather Report 26 March 11
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ጅማ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ሐዋሳ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜን ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በቡልቂ፣ ጊዶሌ፣ ወራቤ፣ ድሬዳዋ እና ፅፅቃ ከ30-57.6 ሚ.ሜ ከባድ ዝናብ ነበራቸው፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ላሬ፣ መንደር 11፣ አዲስ ዘመን፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-41.5°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday the areas of the country that benefited from the belg rains had cloud cover. Along with this, Guji and West Guji, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Jimma, West, Southwest and East Shewa, Hawassa, Wolaita, Gamo, Gofa, South Omo, East Gojam, Waghemra, North Wollo and North Shewa received light to moderate rainfall. In addition, Bulki, Gidole, Warabe, Dire Dawa and Tsitsika received heavy rainfall of 30-57.6 mm. On the other hand, Gambella, Fugendo, Lare, Village 11, Addis Zemen, Semera, Elidar, Gewane, Awash Arba, Kebridehar and Gode recorded the highest temperature of the day at 35-41.5°C
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የተስፋፋ የደመና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ፤ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው መካከለኛ መጠን (ከ11-29ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከኦሮሚያ ክልል የደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜን ሸዋ እና ጅማ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከአማራ ክልል የሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ደቡብ ዞኖች እና ከአፋር ክልል የቅልበቲ፣ ፋንቲ እና ሀሪ ዞኖች ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል። በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ አቦቦ፣ መተማ፣ ቋራ፣ ሠመራ፣ ጎዴ እና ዶሎኦዶ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ እንደሚመዘገብ አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡
Tomorrow, there will be widespread cloud cover over the belg main and second rainy seasons of our country. In addition, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones of the Southern Ethiopian Region; Guji and West Guji, Borena and East Borena zones of the Oromia Region; Bale, Arsi and West Arsi, West and East Hararge zones; All zones of Sidama Region; Gurage, East Gurage, Marekko Special Zone, Silte, Yem Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zones of the Central Ethiopian Region; Bench Sheko, Kefa, Konta and West Omo zones of the Southwestern Ethiopian Region will experience moderate rainfall (11-29mm) in many places. In addition, there will be light rain in the South West, North Shewa and Jimma zones of Oromia region; Addis Ababa; North and South Wollo, North Shewa, Oromo National Special Zone and East Gojam zones of Amhara region; Central, East, South East and South zones of Tigray region and Kelbeti, Fanti and Hari zones of Afar region. Therefore, the amount and distribution of rain will be of great importance for carrying out belg agricultural activities. On the other hand, the maximum temperature of the day will be recorded as 35 to 40 degrees Celsius in Gambella, Abobo, Metema, Quara, Samara, Gode and Doloodo.