Daily Weather Report 26 March 10

Weather Summary for previous day

March 9, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ጅማ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ሐዋሳ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ሰሜን ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በቡልቂ፣ ተርጫ፣ አርባምንጭ፣ ምዕራብ አባያ፣ ጂንካ እና ሳውላ ከ30-53.2ሚ.ሜ ከባድ ዝናብ ነበራቸው፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ላሬ፣ መንደር 11፣ ጨዋቃ፣ ፓዌ፣ ማይሃንሳ፣ የጭላ፣ ሰመራ፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-43.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday the areas of the country that benefited from the belg rains had cloud cover. Along with this, Guji and West Guji, East Bale, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Jimma, West, South West and East Shewa, Hawassa, Wolaita, Gamo, Gofa, South Omo, North Wollo and North Shewa received light to moderate rainfall. In addition, Bulki, Tercha, Arbaminch, West Abaya, Jinka and Saula received heavy rainfall of 30-53.2 mm. On the other hand, Gambella, Fugendo, Lare, Village 11, Chewaka, Pawe, Mayhansa, Yecla, Semera, Gewane, Awash Arba, Semera, Elidar, Kebridehar and Gode recorded the highest temperature of the day at 35-43.0°C.

Weather Forecast for next day

March 11, 2026

በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ፤ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ እና ጅማ ዞኖች፤ በድሬዳዋ፣ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው መካከለኛ መጠን (ከ11-29ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከኦሮሚያ ክልል የደቡብ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ እና ጅማ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከአማራ ክልል የሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ደቡብ ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል። በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ አቦቦ፣ መተማ፣ ቋራ፣ ሠመራ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሀር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል።

Tomorrow, there will be cloud cover in the belg main and second rainy seasons of our country. In addition, in the Southern Ethiopian Region, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; in the Oromia Region, Guji and West Guji, Borena and East Borena; Bale, Arsi and West Arsi, West and East Hararge and Jimma zones; in Dire Dawa, all Sidama Region zones; in the Central Ethiopian Region, Gurage, East Gurage, Marekko Special Zone, Silte, Yem Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zones; The Bench Sheko, Kefa, Konta and West Omo zones of the Southwestern Ethiopian region will receive moderate rainfall (11-29mm) in many areas. In addition, there will be light rainfall in the South West and North Shewa and Jimma zones of Oromia region; Addis Ababa; North and South Wollo, North Shewa, Oromo National Special Zone and East Gojam zones of Amhara region; Central, East, Southeast and South of Tigray region. Therefore, the amount and distribution of rainfall will be of great importance for carrying out belg agricultural activities. On the other hand, the maximum daily temperature in Gambella, Abobo, Metema, Quara, Samara, Gode and Kebridehar will be recorded as 35 to 40 degrees Celsius.