Daily Weather Report 26 March 09
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ በመሆኑም በጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶ፣ ጌዲኦ፣ ሐዋሳ፣ ስለጤ፣ ሀድያ፣ ጉራጌ፣ ቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምስራቅ ሐረርጌ፣ ጅማ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ማይሃንሳ፣ የጭላ፣ መተሃራ፣ ኤሊዳር፣ ሰመራ፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover in the areas of the country that received the autumn rains. Accordingly, in Gamo, Gofa, South Omo, Konso, Gedeo, Hawassa, Selte, Hadia, Gurage, Borena, Gujina and West Guji, Bale, East Hararge, Jimma, West and Southwest Shewa, South Wollo, and North Shewa zones were recived light to moderate (1-29 mm) amount of rainfall. On the other hand, the maximum temperature of the day was recorded at 35-40.8°C in In Gambella, Fugnido, Mayhansa, Yechila, Metehara, Elidar, Semara, Gewane, Awash Arba, Kebridehar and Gode.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች እና ከአማራ ክልል ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በተጨማሪም በውልበርግ፣ ሾኔ፣ ማላጋ፣ ወንዶገነት፣ ኦሞናዳ፣ ሙህርአክሊል፣ እዣ፣ ቆቦ፣ ጉባላፍቶ እና ሀብሩ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በተጨማሪም ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ፋፈን፣ ሲቲ እና ኤረር ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቅልበቲ፣ ፋንቲ፣ ሀሪ እና ጋቢ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ደቡብ ጎንደር እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅና ደቡብ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡በሌላ በኩል በመተማ፣ ሸርኮሌ፣ ኩምሩክ፣ በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል።
Tomorrow, there will be cloud cover and accumulation over areas of the country that experience the main and secondary rainy seasons in Belg. In this regard, from the southern Ethiopian region, the zones of Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo, and Konso; from the Oromia region, the zones of Gujina and West Guji, Borena and East Borena, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Southwest, West, East, and North Shewa; in all the zones of the Sidama region; from the Central Ethiopian region, the zones of Gurage, East Gurage, Mareko, Silte, Yabelo Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata, and Tembaro; from the Southwest region of Ethiopia, the zones of Wolayta, Konta, Dawro, and West Omo; and from the Amhara Region, the zones of North, South Wollo, and North Shewa will experience light to moderate (1-29 mm) rainfall in many places. Additionally, heavy rainfall exceeding 30 mm in 24 hours is expected in Wahlberg, Shone, Malaga, Wondogenet, Omonada, Muhraklil, Ezha, Kobo, Gubalafto, and Habru. Furthermore, in the Oromia region: western and eastern Hararge zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; from the Somali region Dawa, Liben, Afder, Fafen, Siti and Erer zones; Kilbeti, Fanti, Hari, and Gabi zones of the Afar region; from Amhara region Oromo Special Zones, Waghemra, South Gondar, and East Gojam zones; from Tigray region eastern, southeastern, and southern zones will receive light rain. Therefore, the amount and distribution of rainfall will be very important for autumn agricultural activities. On the other hand, in Metema, Sherkole, Kumruk, Gambella, Fugndo, Abobo, Gode, and Kabridehar, the maximum temperature of the day is recorded as 35-40 degrees Celsius.