Daily Weather Report 26 March 08
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ በመሆኑም ቦረናና ምስራቅ ቦረና ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና፣ደቡብ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ፣ ጅማ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ሐዋሳ፣ ባስኬቶ፣ኮንሶ፣ ወላይታ፣ እና ቡርጂ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል ጨዋቃ፣ ላሬ፣ መንደር 11 እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-41.2°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
On the previous day, cloudy conditions observed over Belg benefiting areas of the country. Consequently, the zones of Borena and East Borena, West Guji, Bale, Southwest and North Shewa, Jimma, West Arsi, Hawassa, Basketo, Konso, Wolayta, and Burji received light to moderate rainfall. Meanwhile, in Chewaka, Lare, Mender 11, and Gode, daytime maximum temperatures were recorded between 35 and 41.2°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ እና ከምባታ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ዳውሮ፣ ኮንታ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና እና ምዕራብ አርሲ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ እና ጅማ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከአማራ ክልል የምስራቅ ጎጃም፣ ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ኩምሩክ፣መተማ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ34-40 ዲግሪ ሴልሽየስ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
Tomorrow cloudy skies are expected over regions that are currently in their main and secondary rainy seasons of Belg. In connection with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected over zones of Southern Ethiopia Region including Wolayita,Gamo,Basketo,Gedeo and South Omo; zones of the Sidama Region; from the Central Ethiopia Region the Gurage, Silte, Yem special zone, Hadiya and Kembata zones; and from the Southern West Ethiopia Region the Bench Sheko, Sheka, Keffa, Dawuro, Konta and West Omo zones. In addition, from Oromia Region light rain is expected over Guji and West Guji, Borena and East Borena, West Arsi, South West, West and North Shewa and Jimma zones; Addis Ababa; and from Amhara Region over East Gojjam, South Gondar, North Shewa, and the northern and southern Wollo areas. Meanwhile, temperature forecasts indicate daytime maximum temperatures of about 34–40°C in Gambela, Funyido, Abobo, Kumruk, Metema, Semera, Elidar, Awash Arba, Gewane, Gode and Kebridahar.