Daily Weather Report 26 March 07

Weather Summary for previous day

March 6, 2026

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ በመሆኑም ቦረናና ምስራቅ ቦረና ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምስራቅ ሐረርጌ፣ ሐዋሳ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በያቤሎ፣ ቡርጂ እና ብላቴ ከ30-68.6ሚ.ሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መንደር 11 እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ37-39.5°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday Belg benefiting areas parts of the country had cloudy weather conditions. As a result, Borena and East Borena, Guji and West Guji, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, East Harerge, Hawassa, Gamo, Gofa, South Omo and North Wollo zones received light to moderate rainfall. In addition, Yabelo, Burji and Bilate recorded heavy rainfall amounts ranging from 30 to 68.6 mm. Elsewhere, Gambela, Fugnido, Mender 11 and Gode registered daytime maximum temperatures of 37–39.5°C.

Weather Forecast for next day

March 8, 2026

በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ እና ከምባታ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ዳውሮ፣ ኮንታ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ እና ሊበን ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከኦሮሚያ ክልል የደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ እና ጅማ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከአማራ ክልል የምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ኩምሩክ፣መተማ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ34-40 ዲግሪ ሴልሽየስ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

Tomorrow cloudy conditions are expected over areas that normally frist and second Belg benefiting areas. In connection with this, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected in parts of Southern Ethiopia region: Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Alle, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; in Oromia: Guji and West Guji, Borena and East Borena, West Arsi, Bale and East Bale zones; in all zones of Sidama region; in Central Ethiopia: Gurage, Yem special zone,Hadiya and Kambata zones; in Southwestern Ethiopia region: Bench Sheko, Keffa, Dawuro, Konta and West Omo zones; and in Somali region: Dawa and Liben zones. In addition, light rainfall is expected over parts of Oromia’s Southwest, West and North Shewa and Jimma zones; Addis Ababa; and in Amhara: East Gojjam and North and South Wollo. Meanwhile, daytime maximum temperatures of about 34–40°C are forecast over Gambela, Fugnido, Abobo, Kumruk, Metema, Semera, Elidar, Awash Arba, Gewane, Gode and Kebridahar, according to the meteorological information.