Daily Weather Report 26 March 06
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ በመሆኑም በቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ሐዋሳ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን ፣ ሰሜን ሸዋ እና ደቡብ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአንጋጫ፣ ጊዶሌ፣ ተልተሌ እና ሐረር ከ30-44ሚ.ሜ በላይ ከባድ ዝናብ ነበራቸው፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ጨዋቃ፣ አዲስ ዘመን፣ ማይሃንሳ፣ የጭላ፣ኤሊዳር፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40.5°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the areas of the country that benefited from the belg there was cloud cover. In addition, Borena, Guji and West Guji, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, West, Southwest and East Shewa, Hawassa, Gamo, Gofa, South Omo, North and South Wollo, Oromo National Special Zone, North Shewa and South Tigray received light to moderate rainfall. In addition, Angacha, Gidole, Teltele and Harar received heavy rainfall of more than 30-44 mm. On the other hand, Gambella, Fugendo, Chewaka, Addis Zemen, Mayhansa, Yecla, Elidar, Kebridehar and Gode recorded the highest temperature of the day at 35-40.5°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ፤ አርሲና ምዕራብ አርሲ እና ባሌ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው መካከለኛ መጠን (ከ11-29ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከኦሮሚያ ክልል የደቡብ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ እና ጅማ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከአማራ ክልል የሰሜንና ደቡብ ወሎ ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ኩምሩክ፣መተማ፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ34-40 ዲግሪ ሴልሽየስ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover over the belg main and second rainy seasons of our country. In addition, the Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones of the Southern Ethiopian Region; the Guji and West Guji, Borena and East Borena zones of the Oromia Region; the Arsi and West Arsi and Bale zones of the Central Ethiopian Region; the Gurage, East Gurage, Marekko Special Zone, Silte, Yem Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zones of the Central Ethiopian Region; and the Bench Sheko, Kefa, Konta and West Omo zones of the Southwestern Ethiopian Region will experience moderate rainfall (11-29 mm) in many places. Additionally, light rain will occur in the southwestern and northern Shewa and Jimma zones of the Oromia region; Addis Ababa; and northern and southern Wollo of the Amhara region. On the other hand, numerical forecast indicates that the maximum temperature of the day in Gambella, Fugendo, Abobo, Kumruk, Metema, Awash Arba, Gewane, Gode and Kebridehar will be 34-40 degrees Celsius.