Daily Weather Report 26 March 05
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በመካከለኛው፣ በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምስራቅ ሐረርጌ፣፣ ሐዋሳ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን ፣ ሰሜን ሸዋ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በዶሎመና፣ ግናገር፣ ደብረ ሲና እና ቡልቂ ከ30-60 ሚ.ሜ በላይ ከባድ ዝናብ ነበራቸው፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ጨዋቃ፣ አዲስ ዘመን፣ የጭላ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-38.6°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over the central, southern, southwestern and northeastern parts of the country. Along with this, Borena, Guji and West Guji, Arsi and West Arsi, Bale and East Bale, East Hararge, Hawassa, Southwest and East Shewa, North and South Wollo, Oromo National Special Zone, North Shewa received light to moderate rainfall. In addition, Dolomena, Ginager, Debre Sina and Bulki received heavy rainfall of more than 30-60 mm. On the other hand, Gambella, Chewaka, Addis Zemen, Yecla, Awash Arba, Kebridehar and Gode recorded the highest temperature of the day at 35-38.6°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ፤ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ እና ጅማ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ እና ሊበን ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው መካከለኛ መጠን (ከ11-29ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ እንዲሁም በዶዶላ፣ አዳባ፣ ኮፈሌ፣ ሳውላ፣ ቡልቂ፣ ሶዶ ዙርያ፣ ቦዲቲ እና ሁምቦ፣ ደምቦያ፣ አንጋጫ፣ ዱራሜ በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ደግሞ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በተጨማሪም ከኦሮሚያ ክልል የደቡብ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ እና ጅማ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከአማራ ክልል የሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ደቡብ ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover in the belg main and second rainy seasons of our country. In addition, in the Southern Ethiopian Region, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; in the Oromia Region, Guji and West Guji, Borena and East Borena zones; in Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Jimma; in all Sidama Region zones; in the Somali Region, Dawa and Liben zones; in the Central Ethiopian Region, Gurage, East Gurage, Marekko, Silte, Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zones; The Bench Sheko, Kefa, Konta, and West Omo zones of the southwestern Ethiopian region will receive moderate rainfall (11-29mm) in many places; Dodola, Adaba, Kofele, Saula, Bulki, Sodo Zuria, Boditi and Humbo, Demboya, Angach, Durame will experience heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours at some places. In addition, the Southwest and North Shewa and Jimma zones of Oromia region; Addis Ababa; North and South Wollo, North Shewa, Oromo Nationality Special Zone and East Gojam zones of Amhara region; Our forecast information indicates that there will be light rainfall in the East, Southeast and South of Tigray region.