Daily Weather Report 26 March 04
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በመካከለኛው፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ ጠንካራ የደመና ሽፋን የተስተዋለ ሲሆን፤ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይም የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ሐረር፣ ሐዋሳ፣ አዲስ አበባ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን ፣ ሰሜን ሸዋ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በዲመቃ፣ ቡልቂ፣ ደብረ ሲና እና ያቤሎ ከ30-62 ሚ.ሜ በላይ ከባድ ዝናብ ነበራቸው፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ላሬ፣ መንደር 11፣ አዲስ ዘመን፣ የጭላ፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-40.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, heavy cloud cover was observed in the central, southern and southwestern regions; there was also cloud cover in the northeastern and eastern regions of the country. In connection with this, Borena, Guji and West Guji, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Harar, Hawassa, Addis Ababa, Southwest and East Shewa, North and South Wollo, Oromo National Special Zone, North Shewa received light to moderate rainfall. In addition, heavy rainfall was recorded 30-62 mm in Dimeka, Bulki, Debre Sina and Yabelo. On the other hand, in Gambella, Fugendo, Lare, Village 11, Addis Zemen, Yecla, Awash Arba, Gewane, Kebridehar and Gode, the maximum temperature of the day was recorded at 35-40.8°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ጅማ፤ ሐረር፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ሸበሌ እና ኤረር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው መካከለኛ መጠን (ከ11-29ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ የሚያገኙ ሲሆን፤ በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ደግሞ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ እና ጅማ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከአማራ ክልል የሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover in the belg main and second rainy seasons of our country. In addition, in the Southern Ethiopian Region, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; in the Oromia Region, Guji and West Guji, Borena and East Borena zones; Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Jimma; Harar; in all Sidama Region zones; in the Somali Region, Dawa, Liben, Afder, Shebele and Erer zones; in the Central Ethiopian Region, Gurage, East Gurage, Marekko, Silte, Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zones; The Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, and West Omo zones of the southwestern Ethiopian region will receive moderate rainfall (11-29 mm) in most places, and heavy rainfall of more than 30 mm in a 24-hour period will be experienced in a few places. In addition, the West, Southwest, and North Shewa and Jimma zones of the Oromia region; Addis Ababa; the North and South Wollo, North Shewa, Oromo National Special Zone, and East Gojam zones of the Amhara region; and the Southern zone of the Tigray region will experience light rainfall.