Daily Weather Report 26 March 03

Weather Summary for previous day

March 2, 2026

በትናንትናው ዕለት በመካከለኛው፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ ጠንካራ የደመና ሽፋን የተስተዋለ ሲሆን፤ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይም የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ሐረር፣ ጅማ፣ አዲስ አበባ፣ ሰሜንና ምስራቅ ሸዋ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ደቡብ ትግራይ እና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በዲላ፣ ተርጫ፣ ባቱ እና መቂ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ መንደር 11፣ አዲስ ዘመን፣ የጭላ፣ ሰመራ፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-38.5°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, heavy cloud cover was observed in the central, southern and southwestern parts of the country; there was also cloud cover in the northeastern and eastern parts of the country. In connection with this, light to moderate rainfall was recorded in Borena, Guji and West Guji, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Harar, Jimma, Addis Ababa, North and East Shewa, North and South Wollo, Oromo National Special Zone, North Shewa, South Tigray and South East Tigray. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Dilla, Tercha, Batu and Meki. On the other hand, the maximum temperature of the day was recorded in Gambella, Village 11, Addis Zemen, Yecla, Semera, Awash Arba, Gewane, Kebridehar and Gode.

Weather Forecast for next day

March 4, 2026

በነገው ዕለት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ጅማ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ፣ ዶሎ፣ ፋፈን፣ ሲቲ፣ ጃራር እና ኤረር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ኮንታ፣ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው መካከለኛ መጠን (ከ11-29ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ የሚያገኙ ሲሆን፤ በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ደግሞ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከኦሮሚያ ክልል የምስራቅና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከአማራ ክልል የሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅና ደቡብ ዞኖች እና ከአፋር ክልል የቅልበቲ፣ ፋንቲ፣ ሀሪ እና ጋቢ ዞኖች ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow, there will be strong cloud cover over the belg main and second rainy seasons of our country. In addition, in the Southern Ethiopian Region, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; in the Oromia Region, Guji and West Guji, Borena and East Borena zones; Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Jimma; Harar; Dire Dawa; All zones of Sidama Region; Somali Region’s Dawa, Liben, Afder, Shebele, Korahe, Dolo, Fafen, Siti, Jarar and Erer Zones; Central Ethiopia Region’s Gurage, East Gurage, Marekko, Silte, Yem liyu Zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro Zones; Southwestern Ethiopia Region’s Kaffa, Konta and West Omo Zones will receive moderate rainfall (11-29mm) in many places; and a few places will receive heavy rainfall of more than 30mm in 24 hours. In addition, there will be light rain in the East and North Shewa zones of Oromia region; Addis Ababa; North and South Wollo, North Shewa, Oromo Nationality Special Zone and East Gojam zones of Amhara region; East, Southeast and South zones of Tigray region; and Kelbeti, Fanti, Hari and Gabi zones of Afar region.