Daily Weather Report 26 June27
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ደቡብ ምስራቅ ትግራይ፣ ሀዋሳ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ እና አኝዋክ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በሳውላ 51.2ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በ ጨፋ፣ ጭፍራ፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ እና ሚኤሶ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ36.0-38.4°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were cloudy patches over the western, northwestern, northeastern, eastern, central and southern parts of our country. In addition, light to moderate rainfall was recorded in Jimma, Illubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, East and West Wollega, North, East and South Shewa, Arsi and West Arsi, West Hararghe, North and South Gondar, East Gojjam, North Shewa, North and South Wollo, Southeastern Tigray, Hawassa, Wolaita, Gamo, Gofa, South Omo and Agnuak zones, with heavy rainfall of 51.2 mm recorded at Sawla. Elsewhere, high daytime temperatures ranging from 36.0–38.4°C were recorded in Chefa, Chifra, Diredawa, Metehara and Meiso.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ይበልጥ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሀረር፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ጋቢ እና ሀሪ ዞኖች ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሆሮ ጉዱሩ፣ አዊ ዞን፣ ደቡብ ጎንደር እና ጅማ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጭፍራ፣ መተሐራ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, weather conditions favorable for winter rain will continue to persist and intensify over many areas in the west, north, northwest, northeast, south, southwest and central parts of the country. Accordingly, parts of Oromia including Jimma, Illubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shewa, East and West Hararghe, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, Bale and East Bale, Borena and East Borena zones; Addis Ababa; Harar; zones of Southern Ethiopia Region including Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo and Gedeo; zones of Sidama region; from the Central Ethiopia region: Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, Yem special zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tambaro; from the Southern West Ethiopia region: Keffa, Sheka, Bench Sheko, Konso, Dawuro and West Omo zones; from Afar region: Awsi, Gabi and Hari zones; from Somali region: Fafan zone; from Gambella region: Agnuak and Majang zones; from Benishangul-Gumuz: Asosa, Metekel, Kamashi and Mao-Komo zones; from Amhara region: West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Wag Hemra, North and South Wollo, West and East Gojjam; from the Oromia special zone and North Shewa zones; and from Tigray region: West, Northwest, Northeast, South, Central and Southeast zones — many of these places will receive light to moderate rainfall ranging from 1 to 29 mm. In addition, Horo Guduru, Awi zone, South Gondar and Jimma zones are expected to receive heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours. On the other hand, daytime maximum temperatures of 35 to 40 degrees Celsius will be observed in Semera, Elidar, Gambella, Funyido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhanssa, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Chifra, Metehara, Gode and Kebridahar.