Daily Weather Report 26 June26
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ፣ ሀዋሳ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ምዕራብ ኦሞ እና አኝዋክ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በአዴት 30.0ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ ዳሊፋጌ እና ጭፍራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-44.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were cloudy conditions over the western, northwestern, northeastern, central and southern parts of our country. In addition, Addis Ababa, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, East and West Wollega, North, East, South West and West Shewa, West Arsi, North, South and Central Gondar, Awi zone, West and East Gojjam, Central and Southeastern Tigray, Hawassa, Wolayta Sodo, Western Omo and Agnuak zones received light to moderate rain; in some places heavy rainfall totaling around 30.0 mm was recorded. Elsewhere, high daytime temperatures were observed in Semera, Elidar, Gambella, Funyido, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Dallifage and Cheffa, ranging from 35.0 to 44.8°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የማኦኮሞ ዞን፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጭፍራ፣ መተሐራ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, weather conditions favorable for winter rainfall will persist over western, northern, northwestern, northeastern, southern, southwest and central parts of the country. In connection with this, the following zones will be affected: from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shewa, East and West Hararghe, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, Bale and East Bale, Borena and East Borena; Addis Ababa; Harari; from Southern Ethiopia Region Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo and Gedeo zones; from Sidama region its zones; from Central Ethiopia region Gurage, East Gurage, Mareqo special zone, Silte, Mu special zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tambaro; from Southwest Ethiopia region Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konso, Dawuro and West Omo zones; from Somali region Fafan zone; from Gambela region Agnuak, Itang, Nuer and Majang zones; from Benishangul Gumuz Mao Komo zone; from Amhara region West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Wag Hemra, North and South Wollo, West and East Gojjam; Oromo special zone and North Shewa zones; and from Tigray region West, North West, East, South, Central and Southeastern zones. Many of these areas will receive light to moderate rainfall totaling between 1 and 29 mm. Additionally, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is expected over Jimma and the northern and southern parts of the Gondar zones. Meanwhile, daytime maximum temperatures of 35 to 40 degrees Celsius are forecast in Semera, Elidar, Gambela, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Chifra, Metehara, Gode and Kebridahar.