Daily Weather Report 26 June25

Weather Summary for previous day

June 24, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምስራቅ ጎጃም እና ሰሜን ሸዋ፣ መተከል፣ ጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና አኝዋክ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በፓዌ 33.2ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጭፍራ፣ ፉኝዶ፣ ማይሀንሳ፣ ድሬዳዋ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ36.0-44.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday there were cloudy patches over the western, northwest, northeast, eastern, central and southern parts of our country. In addition, Addis Ababa; northern, southern and central Gondar; Awi Zone; East Gojjam and North Shewa; Metekel; Jimma; Buno Bedele; Horo Guduru; East and West Wollega; East and South West Shewa; Sheka; Bench Sheko; West Omo; and Agnuak zones received light to moderate rainfall, with heavy rain reaching 33.2 mm at Pawe. On the other hand, Semera, Elidar, Chifra, Fugnido, Mayhanssa, Dire Dawa, Awash Arba, Metehara and Kebridahar recorded the day’s highest temperatures, ranging from 36.0 to 44.8°C.

Weather Forecast for next day

June 26, 2026

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ ፣ ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በደቡብ ጎንደር፣ ባሌ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጨፋ፣ ጭፍራ፣ መተሐራ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, weather conditions favorable for winter rainfall will continue in similar fashion over western, northern, northwestern, northeastern, southern, southwest and central parts of the country. In addition, parts of Oromia such as Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shewa, East and West Harerge, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, Bale and East Bale, East Borena zones; Addis Ababa; Harari; from Southern Ethiopia Region the Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo and Gedeo zones; from Central Ethiopia the Gurage, East Gurage, Mareqo special zone, Silte, Yeem special zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tambaro; from South West Ethiopia Peoples’ Region the Keffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro and West Omo zones; from Gambela the Agnuak, Nuer and Majang zones; from Benishangul-Gumuz the Asosa, Metekel, Kamashi and Mao-Komo zones; from Amhara the West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Wag Hemra, North and South Wollo, West and East Gojjam; the Oromia special zones and North Shewa zones; and from Tigray the West, North, Northwest, East, South, Central and Southeast zones will receive light to moderate rainfall amounts ranging from 1 to 29 mm in many of their areas. Furthermore, over South Gondar, Bale and West Arsi zones there will be heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours. On the other hand, in Semera, Elidar, Gambela, Fugnedo, Abobo, Melka Jebdu, Mai Hansa, Mehoni, Dire Dawa, Aisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Chefa, Chifra, Metehara, Gode and Kebridahar daytime maximum temperatures are expected to be high, reaching between 35 and 40 degrees Celsius.