Daily Weather Report 26 June24

Weather Summary for previous day

June 23, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም እና ሰሜን ሸዋ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ ደቡብ ትግራይ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ቤንች ሸኮ፣ አኝዋክ እና ማጃንግ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በጨዋቃ 42.2፣ በመተማ 55.2 እና በመንደር11 36.4 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ ዓለም ከተማ፣ አዋሽ አርባ፣ ከሚሴ፣ ኑራኤራ፣ መተሐራ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-43.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday there were cloud masses over the western, northwestern, northeastern, central and southern parts of the country. In addition, Addis Ababa, western, northern, southern and central Gondar, Awi zone, North and South Wollo, West and East Gojjam and North Shewa, Asosa, Metekel, Southern Tigray, Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kelem, East and West Wellega, North, East and South West Shewa, Bench Sheko, Agnuak and Majang zones received light to moderate rainfall. Heavy rainfall was recorded at Chewaka (42.2 mm), Metema (55.2 mm) and Mender 11 (36.4 mm). Elsewhere, high daytime temperatures ranging from 35.0 to 43.0°C were registered in Semera, Elidar, Fugnido, Melka Jebdu, Mai Hansa, Mehoni, Dire Dawa, Metema, Dallifage, Alem Ketema, Awash Arba, Kemise, Nuraera, Metehara and Kebridahar.

Weather Forecast for next day

June 25, 2026

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ ቡርጂ እና ኮንሶ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በደቡብ ጎንደር እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጨፋ፣ ጭፍራ፣ መተሐራ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, weather conditions favorable for winter rain will persist over many parts of the country, including the western, northern, northwestern, northeastern, southern, southwest and central areas. In addition, rain is expected in parts of Oromia Region Jima, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shewa, East and West Hararghe, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, Bale and East Bale, and Borena and East Borena zones as well as in Addis Ababa and Harari. From the Southern Ethiopia Region: Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Burji and Konso zones will see rain. From Sidama Region zones will also receive rainfall. From the Central Ethiopia Region: Gurage, East Gurage, Mareqo special zone, Silte, Yem special zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tambaro. From the Southwest Ethiopia Region: Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro and West Omo zones. From Gambela Region: Agnuak, Nuer and Majang zones. From Benishangul-Gumuz: Assosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones. From Amhara Region: West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Waghemra, North and South Wollo, West and East Gojjam, the Oromo special zone and North Shewa zones. From Tigray Region: West, North, Northwest, East, South, Central and Southeastern zones. Many of these places will receive light to moderate rainfall, amounting to between 1 and 29 mm. Additionally, in the southern Gondar and western Shewa zones, heavy rainfall exceeding 30 mm is expected within 24 hours. Elsewhere, daytime maximum temperatures of 35 to 40 degrees Celsius will be recorded in Semera, Elidar, Gambela, Funyido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Aisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Chefa, Chifra, Metehara, Gode, and Kebridahar.