Daily Weather Report 26 June23

Weather Summary for previous day

June 22, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአሶሳ፣ መተከል፣ ደቡብ ትግራይ፣ ሰሜን ወሎ፣ አዊ ዞን፤ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ አኝዋክ እና ማጃንግ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በነጆ 39.4፣ በጊምቢ 45.1፣ በበደሌ 39.6፣ በማሻ 30.2፣ በአሺ 30.0 እና በቲንሹ ሜጥ 58.3 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጨፋ፣ ጭፍራ፣ መተሐራ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.8-44.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday there were cloudy patches over the western, northwest, northeast, central and southern parts of our country. In addition, light to moderate rainfall was recorded in the Assosa, Metekel, South Tigray, North Wollo, Awi zone; Jimma, Ilu Aba Bora, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, Agnuak and Majang zones. Heavy rainfall amounts were measured at Nedjo 39.4 mm, Gimbi 45.1 mm, Bedele 39.6 mm, Masha 30.2 mm, Ashe 30.0 mm and Tinshu Metu 58.3 mm. Elsewhere, maximum daytime temperatures ranged from 35.8–44.0°C in Semera, Elidar, Fugnido, Melka Jebdu, Mayhanssa, Mehoni, Dire Dawa, Metema, Dallifage, Awash Arba, Cheffa, Chifra, Metehara and Kebridahar.

Weather Forecast for next day

June 24, 2026

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ይበልጥ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የኖጎብ እና ፋፈን ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በደቡብ ጎንደር ዞን ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጨፋ፣ ጭፍራ፣ መተሐራ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, weather systems favorable for the development of the Kiremt rainfall are expected to remain intensified over the western, northern, northwestern, northeastern, southern, southwestern, and central parts of the country. As a result, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected over many areas of Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru Wollega, Qellem Wollega, East and West Wollega, North Shoa, East Shoa, Southwest Shoa, West Shoa, East and West Hararghe, Arsi, West Arsi, Guji, West Guji, Bale, East Bale, Borena, and East Borena zones of the Oromia region, as well as Addis Ababa; Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Alle, Kore, Gardula, Burji, South Omo, and Konso zones of the South Ethiopia Region; across all zones of the Sidama Region; Nogob and Fafan zones of the Somali region; Gurage, East Gurage, Mareko Special Zone, Silte, Yem Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata, and Tembaro zones of the Central Ethiopia region; Kaffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro, and West Omo zones of the Southwest Ethiopia region; Agnuak and Majang zones of the Gambella region; Assosa, Metekel, and Mao-Komo zones of the Benishangul-Gumuz region; West, North, South, and Central Gondar, Awi, Wag Hemra, North and South Wollo, West and East Gojjam, the Oromo special zone, and North Shoa zones of the Amhara region; and West, North, Northwest, East, South, Central, and Southeast zones of the Tigray region. In addition, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is expected over South Gondar zone. On the other hand, maximum daytime temperatures ranging from 35°C to 40°C are forecast in Semera, Elidar, Gambella, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, May Hansa, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Cheffa, Chifra, Metehara, Gode, and Kebri Dehar.