Daily Weather Report 26 June21
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ሰሜን ጎንደር፣ አኝዋክ እና ቤንች ሸኮ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ ድሬዳዋ፣ ጨፋ፣ ጋምቤላ እና በመተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ36.2-39.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were cloudy patches over the western, northwestern, central and southern parts of the country. Along with that, light to moderate rainfall was recorded in Addis Ababa, Jimma, Iluababora, East Wollega, South West and West Shewa, North Gondar, Agnuak and Bench Sheko zones. On the other hand, very high daytime temperatures ranging from 36.2 to 39.0°C were recorded in Fugnido, Dire Dawa, Cheffa, Gambela and Metehara.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ዝናብ ሰጭ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ቀጣይነት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ ኖጎብ፣ አፍዴር፣ ፋፈን፣ ሲቲ፣ ቆራሄ፣ ኤረር፣ ሸበሌ እና ጃራር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል እና ካማሽ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በምዕራብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ መተከል፣ ቡኖ በደሌ ፣ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ ሸዋ እና ጅማ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጨፋ፣ ጭፍራ፣ መተሐራ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, the rain-bearing weather systems are expected to stay active and persistent across the western, northwestern, southwestern, and central regions of the country. As a result, light to moderate rainfall (ranging from 1 to 29 mm) is anticipated in many areas including Jimma, Illubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru Wollega, Kellem Wollega, East and West Wollega, East, Southwest and West Shoa, East and West Hararghe, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, Bale, Borena, and East Borena zones of the Oromia region; Addis Ababa; Wolayita and Gedeo zones of the South Ethiopia region; all zones of the Sidama region; Dawa, Liben, Nogob, Afder, Fafan, Siti, Korahe, Erer, Shebelle, and Jarar zones of the Somali region; Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, Yem special zone, Hadiya, Halaba, and Kembata Tembaro zones of the Central Ethiopia region; Kaffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, and Dawuro zones of the Southwest Ethiopia region; Agnuak and Majang zones of the Gambella region; Assosa, Metekel, and Kamashi zones of the Benishangul-Gumuz region; and the West, North, South, and Central Gondar, Awi, West and East Gojjam zones of the Amhara Region; along with the Western and Northwestern zones of the Tigray region. Additionally, heavy rainfall, exceeding 30 mm within a 24-hour period is likely to occur, particularly in West Gondar, Awi zone, Metekel, Buno Bedelle, East Wollega, West Shoa, and Jimma zones. On the other hand, maximum daytime temperatures ranging from 35°C to 40°C are expected to be recorded in Semera, Elidar, Gambella, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Cheffa, Chifra, Metehara, Gode, and Kebri Dehar.