Daily Weather Report 26 June20

Weather Summary for previous day

June 19, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ጉራጌ፣ ምዕራብና ሰሜን ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ አኝዋክ እና ማጃንግ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በነቀምቴ 54.7ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ ድሬዳዋ፣ ጨፋ፣ መንደር11 እና በጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.4-38.5°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday there were cloudy conditions over the western, northwestern, central, and southern parts of our country. In association with this, Jimma, Iluababora, East Wollega, West Guji, Gurage, West and North Gondar, Awi Zone, Agnuak and Majang zones received light to moderate rainfall, with Nekemte recording a heavy amount of 54.7 mm. On the other hand, high daytime temperatures of 35.4–38.5°C were recorded in Fugnido, Dire Dawa, Chefa, Mender 11 and Gode.

Weather Forecast for next day

June 21, 2026

በነገው ዕለት ዝናብ ሰጭ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ ኖጎብ፣ ቆራሄ፣ አፍዴር እና ፋፈን ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ እና ቤንች ሸኮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል እና ካማሽ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአዊ ዞን፣ ቡኖ በደሌ እና ጅማ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጨፋ፣ ጭፍራ፣ መተሐራ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, rain-bearing weather systems are expected to persist over the western, northwestern, southwestern, and central parts of the country. In association with this, light to moderate rainfall amounts (1–29 mm) are expected over many areas of Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, East and West Wollega, Southwest and West Shoa, East and West Hararghe, West Arsi, Guji, West Guji, Bale, Borena, and East Borena zones of the Oromia region; Wolayita and Gedeo zones of the South Ethiopia region; all zones of the Sidama region; Dawa, Liben, Nogob, Korahe, Afder, and Fafan zones of the Somali region; Gurage, Yem special zone, Hadiya, Kembata, and Tembaro zones of the Central Ethiopia region; Kaffa, Sheka, and Bench Sheko zones of the Southwest Ethiopia region; Agnuak and Majang zones of the Gambella region; Assosa, Metekel, and Kamashi zones of the Benishangul-Gumuz region; West, North, South, and Central Gondar, Awi zone, and West and East Gojjam zones of the Amhara region; as well as the Western and Northwestern zones of the Tigray region. In addition, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is expected over Awi, Buno Bedelle, and Jimma zones. On the other hand, the maximum temperature is expected to range between 35°C and 40°C in Semera, Elidar, Gambella, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Chefa, Chifra, Metehara, Gode, and Kebri Dehar.