Daily Weather Report 26 June19

Weather Summary for previous day

June 18, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳውሮ፣ ጎፋ፣ ቡርጂ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም እና አኝዋክ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በአይራ 33.5፣ በኦቦመርጋ 91.5 እና በኩሚ 37.7 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ድሬዳዋ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጨፋ፣ ጭፍራ እና መንደር11 የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-47.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday there were clouds over western, northwestern, eastern, central and southern parts of our country. Along with this, heavy rainfall was recorded in Addis Ababa; Harar; Jimma; Ilubabor; Buno Bedelle; Horo Guduru; East and West Wollega; West and Southwest Shewa; Arsi; West Hararghe; Bench Sheko; West Omo; Dawuro; Gofa; Burji; western, northern, southern and central Gondar; Awi Zone; East and West Gojjam; and Agnuak Zones, ranging from light to moderate amounts. Very heavy rainfall amounts of 33.5 mm at Ayira, 91.5 mm at Obomerga and 37.7 mm at Kumi were recorded. Elsewhere, in Semera; Elidar; Gambela; Fugnedo; Melka Jebdu; Dire Dawa; Dallifage; Awash Arba; Cheffa; Chifra and Mender 11, daytime maximum temperatures were recorded between 35.0 and 47.8°C.

Weather Forecast for next day

June 20, 2026

በነገው ዕለት ዝናብ ሰጭ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ ኖጎብ፣ ሲቲ እና ፋፈን ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል እና ካማሽ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ጅማ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጨፋ፣ ጭፍራ፣ መተሐራ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, the rain-bearing weather systems are expected to persist in the western, southwestern, and central parts of the country. In line with this, areas areas including Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shoa, East and West Hararghe, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, Bale, Borena, and East Borena zones in the Oromia region; Addis Ababa; Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, and Gedeo zones in the South Ethiopia region; all zones of the Sidama region; Dawa, Liben, Nogob, Siti, and Fafan zones in the Somali region; Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, Yem special zone, Hadiya, Halaba, Kembata, and Tembaro zones in the Central Ethiopia region; Kaffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, and Dawuro zones in the Southwest Ethiopia region; Agnuak and Majang zones in the Gambella region; Assosa, Metekel, and Kamashi zones in the Benishangul-Gumuz region; the West, North, South, and Central Gondar, Awi, West Gojjam, and East Gojjam zones in the Amhara region; and the western and north western zones of Tigray region are likely to receive light to moderate rainfall, with amounts ranging from 1 to 29 mm in most places.