Daily Weather Report 26 June18
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ሐረርጌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ፣ ጌዴኦ፣ ማዕከላዊ ትግራይ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም እና ጃራር ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ቡኢ፣ ኑራኤራ፣ ድሬዳዋ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጨፋ፣ ሚኤሶ፣ መተሐራ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-44.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were cloudy patches over the western, northwestern, eastern, central, and southern parts of our country. Along with that, Addis Ababa; Harar; Jimma; Ilubabor; Buno Bedelle; Horo Guduru; East Wellega; South West Shewa; East Hararge; Guji and West Guji; Bale and East Bale; Burji; Konso; Gedeo; Central Tigray; West, North, South and Central Gondar; East and West Gojjam; and the Jarar zones recorded light to moderate rainfall. Meanwhile, in Semera, Elidar, Gambella, Funyido, Melka Jebdu, Mayhanssa, Mehoni, Bue, Nura Erer, Dire Dawa, Dallifage, Awash Arba, Chefa, Meiso, Metehara and Gode the daytime maximum temperatures ranged from 35.0°C to 44.8°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ዝናብ ሰጭ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የአርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ ኖጎብ፣ አፍዴር እና ፋፈን ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ማኦኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜን ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ ዞን ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጨፋ፣ ጭፍራ፣ መተሐራ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, rainy weather systems will continue to affect parts of the country in the west, north, northwest, central and south. In connection with this, several zones of Oromia will experience rain: Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shewa, Guji and West Guji, Bale, Borena and East Borena zones. Addis Ababa; from the Southern Ethiopia Region the Wolayita, Gamo and Gedeo zones; zones of the Sidama region; from Somali Region the Dawa, Liben, Nogob, Afder and Fafan zones; from the Centeral Ethiopia region zones of Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, Yeem special zones, Hadiya, Halaba, Kambata and Tambaro zones; from South West Ethiopia the Keffa, Sheka, Bench Sheko, Konta and Dawuro zones; from Gambela the Agnuak and Majang zones; from Benishangul-Gumuz the Assosa, Metekel, Mao Komo and Kamashi zones; from Amhara the West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Waghemra, North Wollo, and West and East Gojjam zones; and from Tigray the West, Northwest and Central zones in many of these places light to moderate rain is expected, totaling between 1 and 29 mm. In addition, the Jimma zone may receive heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours. Elsewhere, high daytime temperatures of 35 to 40 degrees Celsius are expected in Semera, Elidar, Gambela, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhanssa, Mehoni, Dire Dawa, Aisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Cheffa, Chifra, Metehara, Gode and Kebridahar.