Daily Weather Report 26 June17

Weather Summary for previous day

June 16, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ ማዕከላዊ ትግራይ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም እና አኝዋክ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በአርጆ 42.2ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ዴጋን፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ ጨፋ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.4-44.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday there were cloudy patches over the western, northwestern, eastern, central and southern parts of the country. In addition, Addis Ababa; Jimma; Ilubabor; Buno Bedele; Horo Guduru; East and West Wellega; East Shewa; West Hararghe; Asosa; Metekel; Central Tigray; West, North, South and Central Gondar; Awi zone; North and South Wollo; East and West Gojjam; and Agnuak zones received light to moderate rainfall, with heavy rainfall recorded in Arjo measuring 42.2 mm. Meanwhile, in Semera; Elidar; Gambella; Funyido; Melka Jebdu; Degan; Mayhansa; Mehoni; Dire Dawa; Cheffa; Dallifage; Awash Arba; Metehara; Gode; and Kebridahar, daytime maximum temperatures were recorded between 35.4°C and 44.0°C.

Weather Forecast for next day

June 18, 2026

በነገው ዕለት ዝናብ ሰጭ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የአርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ማኦኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ እና በአሶሳ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, rain-bearing weather conditions will continue over the western, northern, northwestern, northeastern, central, and southern parts of our country. In association with this, light to moderate rainfall (1-29mm) will be received in many areas of the following zones: from Oromia region, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, North, Southwest and West Shewa, Guji and West Guji, Bale, Borena and East Borena zones; Addis Ababa; from South Ethiopia region, Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, and Gedeo zones; all zones of Sidama region; from Central Ethiopia region, Gurage, East Gurage, Mareko Special Zone, Silte, Yem Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata, and Tembaro zones; from Southwest Ethiopia Region, Kaffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, and Dawuro zones; from Gambela region, Agnuak and Majang zones; from Benishangul Gumuz, Assosa, Metekel, Mao Komo, and Kamashi zones; from Amhara region, West, North, South and Central Gondar, Awi Zone, Wag Hemra, North and South Wollo, West and East Gojjam zones; and from Tigray region, the West, Northwest, and Central zones. In addition, heavy rainfall exceeding 30mm within 24 hours will occur over Jimma and Assosa zones. On the other hand, the daily maximum temperature will be recorded between 35 and 40 degrees Celsius in Semera, Elidar, Funyido, Abobo, Melka Jebdu, Mai Hansa, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Metehara, Gode, and Kebridahar.