Daily Weather Report 26 June16
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በኢሉባቦር፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ ማዕከላዊ ትግራይ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ አዊ ዞን፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም እና አኝዋክ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በነጆ 35.4፣ በቅዳሜ ገበያ 30.7 እና በኮሶበር 36.1ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አዋሽ አርባ፣ መንደር11፣ አዲስ ዘመን፣ ከሚሴ፣ መተሐራ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-42.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were cloudy patches over western, northwestern, northeastern, central and southern parts of our country. In addition, light to moderate rain fell over Ilubabor, eastern and western Wellega, Asosa, Metekel, central Tigray, western, northern, southern and central Gondar, northern and southern Wollo, Awi Zone, eastern and western Gojjam and Agnuak zones; heavy rainfall was recorded in Nedjo (35.4 mm), Kedame Gebeya (Saturday Market) (30.7 mm) and Kosober (36.1 mm). Elsewhere, in Semera, Elidar, Fugnido, Mehoni, Dire Dawa, Awash Arba, Mender 11, Addis Zemen, Kemise, Metehara and Gode, daytime maximum temperatures were recorded between 35.0 and 42.8°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ዝናብ ሰጭ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ ቀጣይነት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ሰሜን፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሲቲ፣ ሊበን እና ፋፈን ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ማኦኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በምስራቅ ወለጋ፣ ጅማ እና በቡኖ በደሌ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, rain-producing weather disturbances will persist continuously over the western, northwestern, central and southern parts of the country. In connection with this, parts of Oromia including Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Iluababora, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem and the eastern and western Wollega, eastern and western Hararghe, as well as the northern, southern, western and western Shewa zones; from Southern Ethiopia Region the Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo and Gedeo zones; zones in Sidama region; from Somali region the Dawa, Sitti, Liben and Fafan zones; from the Central Ethiopia region Gurage, Silte, the special zone, Halaba, Hadiya, Kembata and Tambaro zones; from Southwest Ethiopia region Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta and Dawuro zones; from Gambela region Agnuak and Majang zones; from Benishangul-Gumuz Asosa, Metekel, Mao Komo and Kamashi zones; from Amhara region the western, northern, southern and central Gondar zones, Awi zone, Wag Hemra, north and south Wollo, and the western and eastern Gojjam zones; and from Tigray region the western, northwestern and central zones many of these areas will receive light to moderate rain (1–29 mm). In addition, the eastern Wollega, Jimma and Buno Bedelle zones are expected to receive heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours. Elsewhere, daytime maximum temperatures between 35 and 40°C will be recorded in Semera, Adigrat, Gambela, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Aisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Metehara, Gode and Kebridahar.