Daily Weather Report 26 June15

Weather Summary for previous day

June 14, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ አዲስ አበባ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ሐረርጌ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ አዊ ዞን፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም እና አኝዋክ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በነቀምቴ 46.5 እና በሸርኮሌ 32.9 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በድሬዳዋ፣ መተሐራ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ጨፋ፣ መሆኒ፣ ማይሀንሳ፣ ውቁሮ፣ ዴጋን፣ አይሻ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.2-40.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday there were cloudy conditions over parts of our country in the west, northwest, northeast, east, central and south. In addition, light to moderate rainfall was recorded in Jimma, Addis Ababa, Iluababora, Buno Bedelle, East and West Wollega, East and Southwest Shewa, East Hararge, West, North, South and Central Gondar, North and South Wollo, Awi Zone, East and West Gojjam, and Agnuak zones. Heavy rainfall was recorded in Nekemte with 46.5 mm and in Sherkole with 32.9 mm. On the other hand, daytime maximum temperatures of 35.2–40.0°C were recorded in Dire Dawa, Metehara, Melka Jebdu, Chefa, Mehoni, May Hansa, Wukro, Degan, Aisha, Kebridahar and Gode.

Weather Forecast for next day

June 16, 2026

በነገው ዕለት ዝናብ ሰጭ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሲቲ፣ ሊበን እና አፍዴር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ማኦኮሞ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, rainy weather systems will persist continuously over western, northwestern, central and southern parts of the country. In connection with this, the following zones will receive light to moderate rainfall (1–29 mm) in many places: from Oromia region Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Iluababora, Bunno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, North, South West and West Shewa zones; from Southern Ethiopia Region Walayita, Gamo, Gofa, Basketo and Gedeo zones; from Sidama region its zones; from Somali region Dawa, Siti, Liben and Afder zones; from Central Ethiopia region Gurage, Silte, the special zone, Hadiya, Kembata and Tambaro zones; from South West Ethiopia region Keffa, Sheka, Bench Sheko, Konta and Dawuro zones; from Gambela region Agnuak and Majang zones; from Benishangul-Gumuz Asosa, Metekel, Mao-Komo and Kamashi zones; from Amhara region West, North, South and Central Gondar, Awi zone, North and South Wollo, West and East Gojjam zones; from Tigray region West, North West and Central zones. Elsewhere, high daytime temperatures between 35 and 40 degrees Celsius will be recorded in places such as Semera, Elidar, Gambela, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Ayisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Metehara, Gode and Kebridahar.