Daily Weather Report 26 June12
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅ ሐረርጌ ፣ ጌዴኦ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ አዊ ዞን እና አኝዋክ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ድሬዳዋ፣ ጭፍራ፣ ጨፋ፣ መንደር11፣ ኑራኤራ፣ መተሐራ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ቡኢ፣ አይሻ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-45.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were cloudy conditions over the western, eastern, central, and southern parts of our country. Along with that, light to moderate rainfall was recorded in Jimma, Illubabor, Buno Bedelle, West and East Wollega, East Hararge, Gedeo, Sheka, Bench Sheko, Awi Zone, and Agnuak Zone. On the other hand, high daytime temperatures ranging from 35.0–45.8°C were recorded in Semera, Elidar, Gambella, Funyido, Dire Dawa, Chifra, Chefa, Mender 11, Nura Era, Metehara, Melka Jebdu, Bui, Aisha, and Gode.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በነገው ዕለት ዝናብ ሰጭ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜን ምዕራብ እና ደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ቀጣይነት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረሪ ክልል፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ ኖጎብ፣ አፍዴር፣ ፋፈን፣ ቆራሄ፣ ሲቲ፣ እና ጃራር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በቡኖ በደሌ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ ምስራቅ ወለጋ እና በምዕራብ ሸዋ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, rainy weather conditions are expected to continue over parts of the country, especially in the western, eastern, northwestern and southern areas. In connection with this, the following zones in Oromia are likely to receive light to moderate rainfall (1–29 mm): Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Illubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, North, South West and West Shewa, and East and West Harerge zones; Harari region; Dire Dawa; and the Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo and Gedeo zones of the Southern Ethiopia region. In the in the Sidama zones. From the Somali Region, the zones of Dawa, Liben, Nogob, Afder, Fafen, Korahe, Sitti and Jarar are included. From Central Ethiopia region: Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, Marko special zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tambaro zones. From the Southwest Ethiopia region: Keffa, Sheka, Bench Sheko, Konta and Dawuro zones. From Gambela region: Agnuak, Itang and Majang zones. From Benishangul-Gumuz: Asosa, Metekel, Kamashi and Mao-Komo zones. From Amhara region: West, North, South and Central Gondar, Awi zone, and West and East Gojjam zones. These areas will see rainfall amounts ranging from light to moderate, about 1–29 mm, in many locations. In addition, the Buno Bedelle, Asosa, Metekel, East Wollega and West Shewa zones may receive heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours. Meanwhile, in Semera, Elidar, Gambella, Funyido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Aisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Metehara, Gode, and Kebridahar, daytime high temperatures are expected to reach between 35 and 40 degrees Celsius.