Daily Weather Report 26 June11
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ጉጂ፣ ባሌ፣ አርሲ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ ፣ ሐረር፤ አሶሳ፣ ጌዴኦ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ጋሞ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ መተከል፣ ፋፈን፣ አኝዋክ፣ ሀዋሳ፣ ደቡብ ወሎ፣ አዊ ዞን እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በጨዋቃ 40.0 እና በጎብዬሬ 70.8ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ዳሊፋጌ፣ ድሬዳዋ፣ ጭፍራ፣ መተሐራ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ማይሀንሳ፣ ቡኢ፣ ከሚሴ፣ ሀራ፣ አዋሽ አርባ፣ አይሻ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-42.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were cloudy conditions over the western, Estern, northwestern, central, and southern parts of our country. In connection with this, light to moderate rainfall occurred in the zones of Jimma, Guji, Bale, Arsi, Illubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, East and West Wollega, South West Shoa, East and West Harerge zones, Harar, Assosa, Gedeo, Sheka, Bench Sheko, Gamo, Gurage, Silte, Metekel, Fafan, Agnuak, Awasa, South Wollo, Awi zone and West Gojjam, with heavy rainfall recorded in Chewaka 40.0 and Gobyere 70.8 mm. On the other hand, daytime maximum temperatures of 35.0–42.0°C were recorded in Semera, Dallifage, Dire Dawa, Chifra, Metehara, Melka Jebdu, Mehoni, Mayhansa, Bui, Kemise, Hara, Awash Arba, Ayisha, Kebridahar and Gode.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ዝናብ ሰጭ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ እና ደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ እና ሊበን ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ እና ከምባታ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ሚኤሶ፣ ኑራኤራ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, rainy weather conditions are expected to persist in the western, northwestern and southern parts of the country. In addition, parts of Oromia Gujii and West Gujii, Borena and East Borena, Bale, West Arsi, Jimma, Iluababora, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, South West and West Shewa, and East Harerge zones; from the Southern Ethiopia region Walayita, Gamo, Gofa and Gedeo zones; Sidama region zones; from Somali region Dawa and Liben zones; from the Central Ethiopia region—Gurage, Yem special zone, Hadiya and Kambata zones; from the Southwest Ethiopia region Kaffa, Sheka, Bench Sheko and Dawuro zones; from Gambela region Agnuak, Itang and Majang zones; from Benishangul Gumuz Assosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones; and from Amhara region West, South and Central Gondar, Awi zone,West and East Gojam zones will receive light to moderate rainfall ranging from 1 to 29 mm in many locations. On the other hand, places such as Semera, Elidar, Gambela, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhanssa, Mehoni, Meiso, Nura Era, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Metehara, Gode and Kebridahar will record high daytime temperatures between 35 and 40 degrees Celsius.