Daily Weather Report 26 June10
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ቦረና፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ሐረር፤ አሶሳ፣ ጌዴኦ፣ መተከል፣ ፋፈን፣ ሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በአርጆ 32.8ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በድሬዳዋ፣ ጭፍራ፣ መተሐራ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ኑራኤራ፣ መሆኒ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ36.6-44.2°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were cloudy conditions over the western, northwestern, central, and southern parts of our country. In connection with this, light to moderate rainfall occurred in the zones of Jimma, Illubabor, East and West Wollega, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, Borena, West and East Hararge, Harar, Assosa, Gedeo, Metekel, Fafan, North and Central Gondar, and East Gojjam, with heavy rainfall recorded in Arjo 32.8 mm. On the other hand, daytime maximum temperatures of 36.6–44.2°C were recorded in Dire Dawa, Chifra, Metehara, Melka Jebdu, Nura Era, Mehoni, Semera, Elidar, Dallifage, Awash Arba, and Gode.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ እና ሊበን ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ሚኤሶ፣ ኑራኤራ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow cloudy skies are expected in the western, northwestern, eastern, central and southern parts of our country. In addition, scattered rain of light to moderate intensity (1–29 mm) is expected in many places of Oromia including West and East Guji, Borena, Bale, West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, South West and West Shewa, West and East Hararghe zones; Harari region; Dire Dawa; from the Southern Ethiopia region Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, and Gedeo zones; all zones of Sidama region; from Somali region Dawa and Liben zones; from the Central Ethiopia region Gurage,Yeem special zone, Hadiya, Kembata and Tembaro zones; from Southern West Ethiopia Keffa, Sheka, Bench Sheko, Konta and Dawuro zones; from Gambela region Agnuak,Itang and Majang zones; from Benishangul-Gumuz Assosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones; and from Amhara region the western,southern and central Gondar zones, Awi zone, and the western and eastern Gojjam zones zone. In another development, daytime maximum temperatures of 35–40 °C are forecast for Semera, Elidar, Gambella, Funyido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Meiso, Nura Era, Dire Dawa, Aisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Metehara, Gode and Kebridahar.