Daily Weather Report 26 June09
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ ፣ አሶሳ፣ ሀዋሳ፣ ቢሾፍቱ፣ ጉራጌ፣ አዊ ዞን እና አኝዋክ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በቅዳሜ ገበያ 48.8 እና በ ነጆ 31.9ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመንደር11፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ድሬዳዋ፣ ጨፋ፣ መተማ፣ መተሐራ፣ አይሻ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-45.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were cloudy patches over the western, northwestern, central and southern parts of the country. In addition, light to moderate rainfall occurred in Jimma, Ilubabor, Horo Guduru, eastern and western Wollega, Guji, Borena, Bale and eastern Bale, Sheka, Bench Sheko, western Omo,Asosa,Awasa,Bishoftu,Gurage,Awi zone and Agnuak zones; heavy rainfall was recorded in Kedame Gebeya with 48.8 mm and in Nedjo 31.9 mm. Elsewhere, in Mender 11, Gambela,Fugnedo, Dire Dawa, Cheffa, Metema, Metahara, Ayisha, Melka Jebdu, Mayhansa, Semera, Elidar, Dallifage, Awash Arba and Gode the daytime maximum temperatures ranged from 35.0 to 45.0°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረሪ ክልል፤ ድሬዳዋ፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ፋፈን እና ሲቲ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የምዕራብ ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ሚኤሶ፣ ኑራኤራ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow cloudy skies are expected in the western, northwestern, eastern, central and southern parts of our country. In addition, scattered rain of light to moderate intensity (1–29 mm) is expected in many places of Oromia including West and East Guji, Borena, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, South West and West Shewa, West and East Hararghe zones; Harari region; Dire Dawa; from the Southern Ethiopia region Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Alaba, Kore, Gardula, Burji and Konso zones; all zones of Sidama region; from Somali region Dawa, Liben,Afder,Fafan and Sitti zones; from the Central Ethiopia region Gurage,Yeem special zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zones; from Southern West Ethiopia Keffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro and West Omo zones; from Gambela region Agnuak and Majang zones; from Benishangul-Gumuz Assosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones; and from Amhara region the western,southern and central Gondar zones, Awi zone, and the western and eastern Gojjam zones;from Tigray region western zone. In another development, daytime maximum temperatures of 35–40 °C are forecast for Semera, Elidar, Gambella, Funyido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Meiso, Nura Era, Dire Dawa, Aisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Metehara, Gode and Kebridahar.