Daily Weather Report 26 June08
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ጉጂ፣ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ፣ ምዕራብ ኦሞ ፣ ምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ ዞን እና አኝዋክ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በቅዳሜ ገበያ 62.6 እና በደምቢ ዶሎ 32.5ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመንደር11፣ ጋምቤላ፣ ድሬዳዋ፣ ጨፋ፣ ሚኤሶ፣ ኑራኤራ፣ መተማ፣ መተሐራ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-44.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were cloudy patches over the western, northwestern, central and southern parts of the country. In addition, light to moderate rainfall occurred in Jimma, Ilubabor, Horo Guduru, Kellem, eastern and western Wollega, Guji, Borena, Bale and eastern Bale, Sheka, Bench Sheko, Dawuro, western Omo, western and central Gondar, western Gojjam, Awi zone and Agnuak zones; heavy rainfall was recorded in Kedame Gebeya with 62.6 mm and in Dembi Dolo with 32.5 mm. Elsewhere, in Mender 11, Gambela, Dire Dawa, Cheffa, Meiso, Nura Era, Metema, Metahara, Semera, Elidar, Dallifage, Awash Arba, Gode and Kebridahar the daytime maximum temperatures ranged from 35.0 to 44.0°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በምዕራብ ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረሪ ክልል፤ ድሬዳዋ፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ ፋፈን እና ሲቲ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ ዞን ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ አዲስ ዘመን፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow cloudy skies are expected in the western, northwestern, eastern, central and southern parts of our country. In addition, scattered rain of light to moderate intensity (1–29 mm) is expected in many places of Oromia including West and East Guji, Borena, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, South West and West Shewa, West and East Hararghe zones; Harari region; Dire Dawa; from the Southern Ethiopia region Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Alaba, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; all zones of Sidama region; from Somali region Dawa, Liben, Fafan and Sitti zones; from the Central Ethiopia region Gurage, Silte, the Yeem special zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zones; from Southern West Ethiopia Keffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro and West Omo zones; from Gambela region Agnuak, Majang and Itang zones; from Benishangul-Gumuz Assosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones; and from Amhara region the western, northern, southern and central Gondar zones, Awi zone, and the western and eastern Gojjam zones. Additionally, heavy rain exceeding 30 mm within 24 hours is expected in the Jimma zone. In another development, daytime maximum temperatures of 35–40 °C are forecast for Semera, Elidar, Gambella, Funyido, Abobo, Melka Jebdu, Addis Zemen, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Aisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Metehara, Gode and Kebridahar.