Daily Weather Report 26 June07

Weather Summary for previous day

June 6, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ ፣ በሰሜን ምዕራብ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ጉራጌ፣ ምዕራብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ሀዋሳ እና ወላይታ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በድሬዳዋ፣ ጨፋ፣ ቀብሪደሃር እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.6-39.6°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday there were cloudy patches over the western, northwestern and southern parts of our country. In addition, light to moderate rainfall was recorded in Jimma, Ilubabor, Gurage, West Gondar, Awi Zone, Hawassa and Walayita zones. On the other hand, in Dire Dawa, Cheffa, Kebridahar and Metehara the daytime maximum temperatures were recorded between 35.6 and 39.6°C.

Weather Forecast for next day

June 8, 2026

በነገው ዕለት በምዕራብ ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ ፣አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረሪ ክልል፤ ድሬዳዋ፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ፋፈን እና ሲቲ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፤ ከትግራይ ክልል የምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአሶሳ፣ መተከል፣ አዊ ዞን፣ ምስራቅ ወለጋ እና ቡኖ በደሌ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ አዲስ ዘመን፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow cloudy skies are expected over the western, northwestern, eastern, central and southern parts of the country. In connection with this, parts of Oromia western and eastern Guji, Borena and eastern Borena, Bale and eastern Bale, Arsi and western Arsi, Jimma, Illubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, eastern and western Wollega, northwestern, southwestern and western Shewa, and western and eastern Hararghe zones Harari region; Dire Dawa; from the Southern Ethiopia Region Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; all zones of Sidama region; from Somali region the Dawa, Fafan and Siti zones; from Central Ethiopia Gurage, Silte, the Yeem special zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tambaro zones; from Southwest Ethiopia region Keffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro and West Omo zones; from Gambela region Agnuak, Majang and Itang zones; from Benishangul-Gumuz Assosa, Metekel, Kamashi and Mao-Komo zones; from Amhara region West, North, South and Central Gondar, Awi zone, and West and East Gojjam; and from Tigray region western and northwestern areas will receive light to moderate rainfall ranging from 1 to 29 mm in many places. In addition, the zones of Assosa, Metekel, Awi zone, eastern Wollega and Buno Bedelle are expected to receive heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours. Meanwhile, in Semera, Elidar, Gambela, Funyido, Abobo, Melka Jebdu, Addis Zemen, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Metehara, Gode and Kebridahar, daytime maximum temperatures are expected to be between 35 and 40 degrees Celsius.