Daily Weather Report 26 June06

Weather Summary for previous day

June 5, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ጎንደር፣ አዊ ዞን እና አኝዋክ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በቅዳሜ ገበያ 58.4ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመንደር7፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ድሬዳዋ፣ አሸሬ፣ ጨፋ፣ ሚኤሶ፣ ኑራኤራ፣ መተማ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-38.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday there were cloudy patches over the western, northwestern, central, and southern parts of our country. Along with this, light to moderate rainfall was recorded in Jima, Ilubabor, Buno Bedelle, East Wellega, Sheka, Bench Sheko, West Gondar, Awi Zone, and Agnuak Zone; on Saturday the market area recorded heavy rainfall of 58.4 mm. On the other hand, in Mandera 7, Gambella, Funyido, Dire Dawa, Ashara, Chefa, Meiso, Nura Era, Metema, and Metahara the daily maximum temperatures were recorded between 35.0 and 38.8°C.

Weather Forecast for next day

June 7, 2026

በነገው ዕለት በምዕራብ ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ ፣አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረሪ ክልል፤ ድሬዳዋ፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ ኖጎብ፣ ፋፈን፣ ሲቲ፣ ኤረር እና ጃራር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኑዌር፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፤ ከትግራይ ክልል የምዕራብ ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በማኦኮሞ፣ ቄለምና ምዕራብ ወለጋ ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ አዲስ ዘመን፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow cloudy skies will affect western, northwestern, eastern, central and southern parts of the country. In addition, rains will occur in many areas of Oromia: Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Iluababora, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, South West and West Shewa, West and East Hararge zones; Harari region; Dire Dawa; from the Southern Ethiopia region the Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Ale, Kore, Gardula, Burji, South Omo and Konso zones; all zones of the Sidama region; from Somali region the Dawa, Liben, Nogob, Fafan, Siti, Erer and Jarar zones; from the Central Ethiopia region Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, Yeem special zone, Hadiya, Halaba, Kebena and Tambaro zones; from South West Ethiopia region the Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro and West Omo zones; from Gambela the Agnuak, Nuer, Majang and Itang zones; from Benishangul Gumuz the Asosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones; from Amhara the West, North, South and Central Gondar and Awi zones, and West and East Gojam; and the Western zone of Tigray many of these places will receive light to moderate rain ranging from 1 to 29 mm. In addition, Mao komo, Kellem and West Wollega may receive heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours. Meanwhile, in Semera, Elidar, Gambella, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Addis Zemen, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Aisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Metehara, Gode and Kebridahar, daytime high temperatures are expected to reach between 35 and 40 degrees Celsius.