Daily Weather Report 26 June05
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ ፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምስራቅ ሐረርጌ፤ አዊ ዞን፣ አሶሳ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጌዴኦ እና አኝዋክ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በመንደር11 94.5 እና በብላቴ 33.8 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመንደር11፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ36.0-43.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were cloudy conditions over the western, eastern, central, and southern parts of our country. At the same time, light to moderate rainfall occurred in Jimma, Buno Bedelle, East and West Wollega, West and south west Shoa, Arsi, Guji and West Guji, East Borena, Bale and East Bale, East Hararge, Awi Zone, Asosa, Bench Sheko, West Omo, Gamo, Gofa, South Omo, Gedeo and Agnuak zones. Heavy rainfall was recorded at Mender 11 (94.5 mm) and Bilate 33.8 mm. On the other hand, high daytime temperatures between 36.0 and 43.8°C were recorded at Mender 11, Semera, Elidar, Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Metehara, Ayshe, Dallifage and Kebridahar.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በምዕራብ ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ ፣አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረሪ ክልል፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር እና ፋፈን ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ እና ከምባታ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኑዌር፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ደቡብ፣ ምዕራብ፣ ማዕከላለዊ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች ፤ ከትግራይ ክልል የምዕራብ ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሸካ ዞን ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ አዲስ ዘመን፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow there will be cloudy cover over western, northwestern, eastern, central and southern parts of our country. In addition, linked to this, heavy rains are expected in various zones of Oromia: Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem; East and West Wollega; South West and West Shewa; West and East Hararghe zones; Harari region; and from the Southern Ethiopia region: Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo and Gedeo zones; all zones of Sidama region; from Somali region: Dawa, Liben, Afder and Fafan zones; from the Central Ethiopia region: Gurage, the Special Mello zone, Hadiya, Halaba and Kambata zones; from the Southwest Ethiopia Region: Keffa, Sheka, Bench Sheko, Konta and Dawuro zones; from Gambela region: Agnuak, Nuer, Majang and Itang zones; from Benishangul-Gumuz: Asosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones; from Amhara region: West and East Gojjam, Awi zone, South, West, Central and South Gondar zones; and from Tigray region the Western zone many of these places will receive light to moderate rainfall ranging from 1 to 29 mm. Additionally, in the Sheka zone there will be heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours. Elsewhere, in Semera, Elidar, Gambela, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Addis Zemen, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Aisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Metehara, Gode and Kebridahar, daytime maximum temperatures are expected to be high, registering between 35 and 40 degrees Celsius.