Daily Weather Report 26 June04
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ ፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፤ ማዕከላዊ ጎንደር፣ ደቡብ ወሎ፣ ጌዴኦ፣ ሸካ፣ ጎፋ፣ ጉራጌ እና አኝዋክ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ሰመራ፣ ኤሊዳር፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ፣ አይሻ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-42.6°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there was a haze of clouds over the western, eastern, central and southern parts of the country. In connection with this, light to moderate rainfall was recorded in the zones of Jimma, Ilu Aba Bora, Buno Bedelle, Horo Guduru, East and West Wollega, West Shewa, Arsi, West Guji, Borena and East Borena, East Bale, West and East Hararghe, central Gondar, South Wollo, Gedeo, Sheka, Gofa, Gurage and Agnuak. On the other hand, high daytime temperatures ranging from 35.0 to 42.6°C were recorded in Gambela, Funyido, Semera, Elidar, Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Metehara, Aysha, Dallifage, Awash Arba and Kebridahar.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በምዕራብ ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና፣ ባሌ ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለምና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረሪ ክልል፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ እና ከምባታ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የአዊ ዞን፣ ምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች ፤ ከትግራይ ክልል የምዕራብ ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ አዲስ ዘመን፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መተሐራ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow clouds, fog and mist will be present over western, northwestern, eastern, central and southern parts of the country. In addition, Oromia regions including Guji and West Guji, Borena, Bale, West Arsi, Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Kelem and West Wollega, and West and East Hararghe zones; Harari region; from South Ethiopia the zones of Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo and Gedeo; all zones of Sidama region; the Fafan zone of Somali region; from Centeral Ethiopia region Hadiya and Kambata zones of; from Southwest Ethiopia the region the zones of Kefa, Sheka, Bench Sheko, Konta and Dawuro; from Gambela the Agnuak, Majang and Itang zones; from Benishangul-Gumuz the Asosa, Metekel, Kamashi and Mao-Komo zones; from Amhara the Awi zone and the western and central Gondar zones; and the western zone of Tigray many of these places will receive light to moderate rainfall ranging from 1 to 29 mm. Elsewhere, in Semera, Elidar, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Addis Zemen, Mayhansa, Mehoni, Metema, Dallifage, Awash Arba, Metehara, Gode and Kebridahar, daytime maximum temperatures will be high, reaching about 35 to 40 degrees Celsius.