Daily Weather Report 26 June03
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ፣ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፤ ሐረር፤ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ መተከል፣ ጌዴኦ፣ ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጉራጌ እና አኝዋክ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በውልበርግ 31.4 እና በቻግኒ 32.4 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መተሐራ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ እና አዋሽ አርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-38.4°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
On the previous day there were widespread clouds over the western, northwestern, eastern, central and southern parts of the country. Along with this, light to moderate rainfall was recorded in Jimma, Iluababora, Buno Bedelle, Horo Guduru, East and West Wollega, East Shewa, Arsi, Guji, Borena and East Borena, East Bale, West and East Hararghe, Harari, South and Central Gondar, West and East Gojjam, Awi zone, Metekel, Gedeo, Bench Sheko, Dawuro, West Omo, Walayita, Gofa, South Omo, Gurage and Agnuak zones. Heavy rainfall amounts of 31.4 mm and 32.4 mm were recorded at Wulbarg and Chagni respectively. On the other hand, in Semera, Elidar, Melka Jebdu, Metehara, Mayhansa, Mehoni and Awash Arba, the daytime maximum temperatures ranged from 35.0 to 38.4°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በምዕራብ ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጌዴኦ፣ አሌ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን እና አፍዴር ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኑዌር፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ፤ ከትግራይ ክልል የምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአሶሳ እና በኢሉባቦር ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ አዲስ ዘመን፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ ፣ አዋሽ አርባ ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow there will be cloudy skies across western, northwestern, eastern, central, and southern parts of the country. In line with this, the following zones will receive light to moderate rainfall (1–29 mm): from Oromia region West Guji, Guji, Borena and East Borena, Bale and East Bale, West Arsi, Jimma, Ilu Aba Bora, Bunno Bedele, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, South, Southwest and West Shewa, and East and West Harerge zones; from Southern Ethiopia Region Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Gedeo, Alaba, Konta, Gardula, Burji, South Omo, and Konso zones; all zones of Sidama region; from Somali region Dawa, Liben, and Afder zones; from Central Ethiopia region Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, Mu special zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zones; from South West Ethiopia region Keffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro and West Omo zones; from Gambela region Agnuak, Nuer, Majang and Itang zones; from Benishangul-Gumuz Asosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones; from Amhara region West, North, South and Central Gondar, West and East Gojjam, Awi zone, North and South Wollo, the Oromia Special Zone, North Shewa and Wag Hemra; and from Tigray region Western and Northwestern zones, where many places will see light to moderate rainfall (1–29 mm). In addition, heavy rainfall exceeding 30 mm in 24 hours is expected in Asosa and Ilu Aba Bora zones. Elsewhere in Semera, Elidar, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Addis Zemen, Mayhansa, Mehoni, Metema, Dallifage, Awash Arba, Gode and Kebridahar, daytime maximum temperatures are expected to be between 35 and 40 degrees Celsius.