Daily Weather Report 26 June 30
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን ሸዋ፣ ዋግኸምራ፣ ቤንች ሸኮ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ እና ጉራጌ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ ሚኤሶ፣ ጭፍራ፣ ጨፋ፣ ባቲ፣ ዳሊፋጌ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.5-42.1°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were cloudy patches over the western, northwestern, northeastern, central and southern parts of our country. In addition, Addis Ababa, Jimma, Ilubabor, the eastern and western Wollega, North, East and South Wollo, Shewa North, West and East Gojam, Awi Zone, North and Central Gondar, North Shewa, Wag Hemra, Bench Sheko, Central and Southeastern Tigray and Gurage zones recorded light to moderate rain. On the other hand, high daytime temperatures ranging from 35.5°C to 42.1°C were recorded at Funyido, Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Aisha, Meiso, Chifra, Chefa, Bati, Dallifage and Kebridahar.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ከሚሴ፣ ጭፍራ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, weather conditions favorable for winter rain will continue in similar patterns across western, northern, northwestern, northeastern, southern, southwest and central parts of the country. In addition, parts of Oromia including Jimma, Iluababora, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shewa, East and West Hararghe, Arsi and West Arsi, Bale, Guji and West Guji zones as well as Addis Ababa; zones of South Ethiopia such as Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo and Gedeo; zones of Sidama; from the Centeral Ethiopia region the Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, Yem special zone, Hadiya, Halaba, Kembata and Tembaro zones; from the Southwest Ethiopia region the Kaffa, Sheka, Bench Sheko, Konta and Dawuro zones; from Gambella the Agnuak and Majang zones; from Benishangul Gumuz the Assosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones; from Amhara the West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Wag Hemra, North and South Wollo, West and East Gojjam and North Shewa zones; and from Tigray the West, Northwest, Northeast, South, Central and Southeast zones many places in these areas will receive light to moderate rainfall ranging from 1 to 29 mm. Furthermore, the Jimma, Southwest and West Shewa zones will experience heavy rain exceeding 30 mm within 24 hours. Elsewhere, places such as Semera, Elidar, Gambella, Funyido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Aisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Kemise, Cheffa and Metehara will record daytime maximum temperatures between about 35 and 40 degrees Celsius.