Daily Weather Report 26 June 29
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ሀዋሳ፣ አሶሳ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን ሸዋ፣ ዋግኸምራ፣ ጉራጌ፣ ጎፋ፣ ወላይታ፣ አኝዋክ፣ ማጃንግ፣ ማዕከላዊ ትግራይ እና ቤንች ሸኮ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በቡሬ 37.8 እና በአሺ 38.0 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ አዋሽ አርባ፣ ጭፍራ፣ ጨፋ፣ ባቲ፣ ከሚሴ፣ መተሐራ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-45.2°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were cloudy patches over the western, northwestern, eastern, central, and southern parts of our country. In connection with this, Addis Ababa; Hawassa, Asosa, Ilubabor, Buno Bedelle, East and West Wollega; North, East and South West Shewa; Arsi and West Arsi; West and East Gojjam; North and Central Gondar; North Shewa; Wag Hemra; Gurage; Gofa; Wolayita; Agnuak; Majang; Central Tigray; and Bench Sheko zones received light to moderate rainfall, while heavy rainfall 37.8 mm in Bure and 38.0 mm in Ashe was recorded. On the other hand, in Semera, Elidar, Gambella, Funyido, Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Aisha, Metema, Awash Arba, Chifra, Chefa, Bati, Kemise, Metehara, and Kebridahar, the daytime maximum temperatures were recorded between 35.0 and 45.2°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሀረር፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ ጎጃም፣ መተከል፣ ቡኖ በደሌ እና ሆሮ ጉዱሩ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጭፍራ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, the weather systems favorable for the formation of the Kiremt rainfall are expected to remain strong over the western, northern, northwestern, northeastern, eastern, southern, southwestern, and central parts of the country. In association with this, light to moderate rainfall, ranging from 1 to 29 mm, is anticipated in many areas including Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru Wollega, Kellem Wollega, East and West Wollega, as well as North, East, Southwest, and West Shoa, East and West Hararghe, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, Bale and East Bale, Borena and East Borena in the Oromia region; Addis Ababa; Harari region; and the zones of Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, and Gedeo in South Ethiopia; all zones of Sidama region; the Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, Yem special zone, Hadiya, Halaba, Kembata, and Tembaro zones in the Central Ethiopia region; Kaffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawuro, and West Omo zones in the Southwest Ethiopia region; Agnuak, Itang, Nuer, and Majang zones in the Gambella region; Assosa, Metekel, Kamashi, and Mao-Komo zones in the Benishangul-Gumuz region; will have it in. West, North, South, and Central Gondar, Awi, Wag Hemra, North and South Wollo, West and East Gojjam, and North Shoa zones in the Amhara region; and West, Northwest, East, South, Central, and Southeast zones in the Tigray region. Additionally, some areas like Jimma, Awi, West Gojjam, and Metekel, Buno Bedele, and Horo Guduru zones are expected to receive heavy rainfall, exceeding 30 mm within a 24-hour period. Meanwhile, daytime maximum temperatures are forecasted to be recorded between 35°C and 40°C in places like Semera, Elidar, Gambella, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Ayesha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Chifra and Metehara.