Daily Weather Report 26 June 28

Weather Summary for previous day

June 27, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ሀዋሳ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜንና ምስራቅሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን ወሎ፣ ጉራጌ፣ ሸካ እና ቤንች ሸኮ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በባህርዳር 56.4 እና በሾላ ገበያ 32.7ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጨፋ፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ እና ሚኤሶ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-38.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover in the western, northwestern, eastern, central and southern parts of our country. In this regard, in Addis Ababa, Hawassa, Ilubabor, Horo Guduru, East and West Wellega, North and East Shewa, Arsi and West Arsi, West Hararge, East Gojjam, North Shewa, North Wollo, Gurage, Sheka and Bench Sheko zones received light to moderate rainfall. Additionally, in Bahir Dar 56.4 mm and Shola Gebeya 32.7 mm heavy rainfall were recorded.

Weather Forecast for next day

June 29, 2026

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ፣ ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ይበልጥ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሀረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዴኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የሀሪ ዞን፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን ሲቲ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የመተከል እና ካማሽ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ጉራጌ እና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጭፍራ፣ መተሐራ እና ቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, weather systems favorable for the Kiremt-season rainfall will continue to strengthen over the western, northern, northwestern, northeastern, eastern, southern, southwestern, and central parts of the country. Accordingly, in Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, East and West Wellega, North Shewa, East Shewa, Southwest Shewa, West Shewa, East and West Hararge, Arsi, West Arsi, Guji, West Guji, Bale, East Bale, Borena, and East Borena Zones of Oromia Region; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; Welayita, Gamo, Gofa, Basketo, and Gedeo Zones of South Ethiopia Region; all zones of Sidama Region; Gurage, East Gurage, Mareko Special Zone, Silte, Yem Special Zone, Hadiya, Halaba, Kembata, and Tembaro Zones of Central Ethiopia Region; Kaffa, Sheka, Bench Sheko, Konta, Dawro, and West Omo Zones of Southwest Ethiopia Region; Hari Zone of Afar Region; Fafen and Siti Zones of Somali Region; Agnuwak and Majang Zones of Gambella Region; Metekel and Kamashi Zones of Benishangul-Gumuz Region; West, North, South, and Central Gondar, Awi Zone, Waghemra, North and South Wollo, East and West Gojjam, Oromo Special Zone, and North Shewa Zones of Amhara Region; and the Western, Northwestern, Eastern, Southern, Central, and Southeastern Zones of Tigray Region are expected to receive light to moderate rainfall (1–29 mm). In addition, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is expected over Jimma, Awi Zone, West Gojjam, Gurage, and Southwest Shewa Zones. On the other hand, the daily maximum temperature is expected to range between 35°C and 40°C in Semera, Elidar, Gambella, Fugnido, Abobo, MelkaJebdu, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Aisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Chifra, Metehara, and Kebridahar.