Daily Weather Report 26 July 28
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ ማጃንግ፣ አኝዋክ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ፣ ሰሜን ሸዋ፣ አውሲ፣ ጉራጌ፣ ምስራቅ እና ማዕከላዊ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በማሻ 30.0፣ በአሸሬ 31.1፣ በሀሮ 30.4፣ በደብረ ሲና 35.1፣ በዳሊፋጌ 38.2 እና በደብረማርቆስ 30.0 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ በመልካ ጀብዱ፣ ድሬዳዋ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ፣ ኑራኤራ፣ መተሐራ፣ ከሚሴ፣ ቀብሪደሃር እና ፉኝዶ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-43.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, widespread cloud cover and wind were observed across the western, northern, northwestern, northeastern, central, and southern parts of our country. In addition, in Addis Ababa; Dire Dawa; in the Sidama region zones; Jimma, Ilubabor, Horogudru, Kellem, the eastern and western Wellega, the north, the east, the south-western and West Shoa, West Harerge, Bench Shako, Kefa, Asosa, Metekel, Majang, Agnuak, the Centeral, northern and southern Gondar, Awi zone, Waghemra, the northern and southern Wallo, Oromo ethnic zone,North Shoa, Awusi, Gurage, Eastern and Central Tigray regions, moderate to heavy rainfall was recorded. In Masha 30.0 mm, in Ashere 31.1 mm, in Haro30.4 mm, in Debre Sina 35.1 mm, in Dallifage38.2 mm, and in Debre Markos 30.0 mm heavy rainfall Recorded. On the other hand, in Semera, Elidar, Melka Jebdu, Dire Dawa, Dallifage, Awash Arba, Gode, Nuraera, Matahera, Kemise, Kebridahar, and Fugnedo, daily maximums temperatures ranging from 35.0 to 43.8°C recorded.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረሪ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ጋሞ፣ ጎፋ እና ጌዴኦ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአሶሳ፣ መተከል፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ ጎንደር፣ ሰሜን ምዕራብ ትግራይ፣ ጉራጌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩና ምስራቅ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር እና ጭፍራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, weather condition that is suitable for winter is expected to occur with similarly due to atmospheric instability in the north, northwest, northern west, northeast, east, southwest, and the central parts of our country. In associated with Oromia region, Jimma, Ilubabor, Bono, Horo Guduru, Kellem, East and West Wellega, West, North, East and South West Shoa, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, West and East Hararghe; Addis Ababa; Dire Dawa; Harari; West, Centeral,North and south Gondar, East and West Gojam, North and south Wallo, Oromo ethnic zone and North Shoa zones; from the Tigray region in the northwest, north, east, central and southern areas, and from the Gambela region in the Agnuak, Itang, and Majang zones; from Benishangul-Gumuz in Assosa, Metekel, Kamashi and Mankato zones; from Afar region in Awusi, Kilbeti, Gabi and Hari zones; from Somalia region in Siti and Fafen zones; from central Ethiopia in Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silt’e, Yem special zone, Hadiya, Kembata and Tembaro zones; From the Southwestern Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Keffa, West Omo,Konta and Dawuro zones; Sidama regional zones; from the Southern Ethiopia region, the Walayita zone, from the Southern Ethiopia Wolayita,Gamo,Gofa and Gedeo Zones in many areas from light to moderate rainfall (ranging from 1-29 millimeters) is expected. In addition, in the Assosa, Metekel, East and West Gojam, Awi zone,West Gondar, South west Tigray, Gurage, Kellem, Horo Guduru and West Wellega, West, and South West Shoa there will be heavy rainfall of more than 30 millimeters within 24 hours. On the other hand, in the Semera, Elidar, Fugnedo, Abobo, Melka Jebdu, Mehoni, Diredawa, Ayisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Kebridahar, Gode, and Chifra daytime maximum temperatures ranging from 35 to 40 degrees Celsius are anticipated.