Daily Weather Report 26 July 27
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በሲዳማ ክልል ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌና ባሌ ምስራቅ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳውሮ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ ማጃንግ፣ አኝዋክ፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ አውሲ፣ ፋንቲ፣ ምስራቅ እና ማዕከላዊ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በሀዋሳ 56.7፣ በአዴት 36.0፣ በኦሞናዳ 30.5፣ በባቱ 67.5፣ በአርሲ ሮቤ 40.0፣ በአቄስታ 30.6፣ በሽሬ እንዳስላሴ 39.1 እና በባምባሲ 45.2ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ በመልካ ጀብዱ፣ መሆኒ፣ አይሻ፣ ቀብሪደሃር፣ ባቲ፣ ሸርኮሌ፣ አዋሽ አርባ እና ፉኝዶ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-42.6°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
During yesterday, widespread cloud cover and wind were observed across the western, northern, northwestern, northeastern, central, and southern parts of our country. In addition, in the Sidama region and its zones, as well as in Addis Ababa, Jimma, Ilubabor, Horogudru, Kellem, the eastern and western lowlands, the north, the east, the south-western areas, Harerge, Bale, Bale East, West Arsi, Sheka, Bench Shako, Kefa, western Omo , Dawuro, Walayita, Gamo, Asosa, Metekel, Majang, Agnuak, the northern and southern Gondar, Awi zone, Waghemra, the northern and southern Wallo, Eastern and Central Tigray regions, moderate to heavy rainfall was recorded. Rainfall totals reached 56.7 mm in Hawassa, 36.0 mm in Adet, 30.5 mm in Omo Nada, 67.5 mm in Batu, 40.0 mm in Arsi Robe, 30.6 mm in Akesta, 39.1 mm in ShireEndasilasse, and 45.2 mm in Bambasi, all indicating substantial precipitation. On the other hand, in Semera, Elidar, Meze Mole, Mehoni, Aisha, Kebridahar, Bati, Sherkole, Awash Arba, and Fugnedo, temperatures recorded high daily maximums ranging from 35.0 to 42.6°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ እና ባሌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረሪ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ጋቢ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ጋሞ፣ ጎፋ እና ጌዴኦ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በምዕራብ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሸካ፣ ማጃንግ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር፣ ጎዴ፣ ጭፍራ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, weather condition that is suitable for winter is expected to occur with similarly due to atmospheric instability in the north, northwest, northern west, northeast, east, southwest, and the central parts of our country. In associated with Oromia region, Jimma, Ilubabor, Bono, Haro Guduru, Kellem, East and West Wellega, West,North,east and South Shoa, West and East Hararghe, Arsi and West Arsi Guji, Addis Ababa; Dire Dawa; Harari; West, Centeral,North and south Gondar, East and West Gojam, North and south Wallo, Oromo ethnic zones and North Shewa zones; from the Tigray region in the northwest, north, east, central and southern areas, and from the Gambela region in the Agnuak, Itang, and Majang zones; from Benishangul-Gumuz in Assosa, Metekel, Kamashi and Mankato zones; from Afar region in Awusi, Gabi and Hari zones; from Somalia region in Siti and Fafen zones; from central Ethiopia in Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silt’e, Yem special zone, Hadiya, Kembata and Tembaro zones; From the Southwestern Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Keffa, West Omo,Konta and Dawuro zones; Sidama regional zones; from the Southern Ethiopia region, the Walayita zone, from the Southern Ethiopia Wolayita,Gamo,Gofa and Gedeo Zones in many areas from light to moderate rainfall (ranging from 1-29 millimeters) is expected. In addition, in the western Gojjam, Jimma, Ilubabor, Bunno Bedele, Sheka, Majang and Eastern Wellega there will be heavy rain of more than 30 millimeters within 24 hours. On the other hand, in the Semera, Elidar, Gambella, Fugnedo, Abobo, and Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Diredawa, Ayisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Kebridahar, Gode, Chifra, and Metahara, high temperatures ranging from 35 to 40 degrees Celsius are anticipated.