Daily Weather Report 26 July 26

Weather Summary for previous day

July 25, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በሲዳማ ክልል ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሸካ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በላሊበላ 90.0፣ በነፋስ መውጫ 48.7፣ በወገል ጤና 40.0፣ በወረኢሉ 46.0፣ በሲሪንቃ 30.5፣ በጨፋ 60.0፣ በአምባ ማሪያም 38.6፣ በመካነ ሰላም 35.2፣ በደብረ ወርቅ 52.8 እና በጊምቢ 50.4 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በድሬዳዋ፣ ጎዴ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.6-36.2°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, in the western, northern eastern, northern western, eastern, central, and southern parts of our country, there was rainfall. In addition, together with this, in the Sidama region zones, Addis Ababa, Diredawa, Ilubabor, Bunno Bedele, eastern and western Wellega, Sheka, West, Centeral,North and south Gondar, Awi zone, Waghemra, northern Shewa, Gurage, Silte, southern east and southeast Tigray zones, light to moderate rainfall was recorded. The rainfall intensities were as follows: 90.0 mm in Lalibela, 48.7 mm in the Nefasmewcha, 40.0 mm in Wegeltena, 46.0 mm in Wereilu, 30.5 mm in Sirinka, 60.0 mm in Chefa, 38.6 mm in AmbaMariyaam, 35.2 mm in Mekane Selam, 52.8 mm in Debre Werk, and 50.4 mm in Gimbi. Significant rainfall was recorded in those areas. Separately, in Dire Dawa, Gode, and Metehara the maximum temperatures reached 35.6–36.2°C.

Weather Forecast for next day

July 27, 2026

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ይበልጥ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ እና ባሌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረሪ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ጋቢ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምስራቅ ጎጃም፣ አሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ ፣ ማኦኮሞ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር፣ ጎዴ፣ ጭፍራ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

On the upcoming day, rainfall that is suitable for Winter is expected to occur with increasing intensity due to atmospheric instability in the north, northwest, northern west, northeast, east, southwest, and the central parts of our country. In associated with Oromia region, Jimma, Ilubabor, Bono, Haro Guduru, Kellem, East and West Wellega, West,North,east and South Shoa, West and East Hararghe, Arsi and West Arsi Guji, Addis Ababa; Dire Dawa; Harari; West, Centeral,North and south Gondar, East and West Gojam, North and south Wallo, Oromo ethnic zones and North Shewa zones; from the Tigray region in the northwest, north, east, central and southern areas, and from the Gambela region in the Agnuak, Itang, and Majang zones; from Benishangul-Gumuz in Assosa, Metekel, Kamashi and Mankato zones; from Afar region in Awusi, Gabi and Hari zones; from Somalia region in Siti and Fafen zones; from central Ethiopia in Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silt’e, Yem special zone, Hadiya, Kembata and Tembaro zones; From the Southwestern Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Keffa, West Omo,Konta and Dawuro zones; Sidama regional zones; from the Southern Ethiopia region, the Walayita zone, from the Southern Ethiopia Wolayita Zone in many areas from light to moderate rainfall (ranging from 1-29 millimeters) is expected. In addition, in the western, northern, southern, and central Gondar, Eastern Gojjam, Assosa, Metekel, Kamashi, Mao Komo, western Shoa, Jimma, Ilubabor, Bunno Bedele, Kelem, Eastern and western Wellega, there will be heavy rain of more than 30 millimeters within 24 hours. On the other hand, in the Semera, Elidar, Gambella, Fugnedo, Abobo, and Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Diredawa, Ayisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Kebridahar, Gode, Chifra, and Metahara, high temperatures ranging from 35 to 40 degrees Celsius are anticipated.