Daily Weather Report 26 July 25
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በሲዳማ ክልል ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ሸካ፣ ዳውሮ፣ ወላይታ፣ መተከል፣ ማጃንግ፣ አኝዋክ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ፣ ጉራጌ እና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በደብረ ብርሃን 48.3፣ በአንጋር ጉቲን 40.0፣ በቲንሹ ሜጢ 37.2 እና በ አባይ ሸልኮ 32.2 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በድሬዳዋ፣ መተማ፣ ጎዴ፣ ሲቦ፣ ፉኝዶ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-37.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
During yesterday, in the western, northern, eastern, central, and southern parts of our country, there were cloudy conditions. In line with this, in the Sidama region’s zones, including Addis Ababa, Dire Dawa, Ilubabor, Horogudru, eastern and western Wellega, northern,eastern,South western and west Shoa, Shakka,Dawuro,Walayita,Metekel,Majang,Agnuak, western, northern, southern, and central Gondar, Awi zone, Waghemra, northern and southern Wollega, western and eastern Gojjam, Oromo Ethnic special zones, northern Shoa, Gurage, and eastern Tigray, rainfall ranged from light to moderate amounts. Specifically, the rainfall amounts recorded were 48.3 mm in Debre Birhan, 40.0 mm in Angar Gutin, 37.2 mm in Tinshu Meta, and 32.2 mm in Abay Shelko. In other areas such as Dire Dawa, Metema, Gode, Sibo, Fugnedo, and Metahara, high daytime temperatures reached between 35.0–37.0°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ እና ባሌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረሪ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሰሜንና ምስራቅ ሸዋ፣ ሰሜን ምዕራብ ትግራይ፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር፣ ጎዴ፣ ጭፍራ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
On the following day, there will be rain for Christmas in weather conditions suitable for that purpose. The disturbances will persist across the north, west, northwest, northeast, southeast, and southwest, and throughout our central regions. Associated with this, from the Oromia region and the zones of Jimma, Ilubabor, Bono Bedele, Horogudru, Kellem, the eastern and western Wellega, the north, the east, the southwestern and western Shoa, Arsi and western Arsi, the western and eastern Hararghe, and the Bale zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harari; and in Amhara Region the western, northern, central, eastern, and southern Gondar,Awi zone,Waghemra,North and South Wallo,West and East Gojjam,Oromo Ethnic special zone and North Shoa; West,North west,East,Centeral,South and South East of Tigray region , the Agnuak and Majang zones of Gambela Region; in Benishangul-Gumuz the Assosa, Metekel, Kamashi, and Mao komo zones; in Afar Region the Awsi, Kilbeti, Gabi, and Hari zones; in Somalia Region the Sitti and Fafan zones; in the central Ethiopia region the Gurage, eastern Gurage, Marako special zone; Silt’e, Yem special zone, Halaba, Hadiya, from Mille and Tara zones; in the Southern Western Ethiopia region the Shaka, Bench Shako, Keffa, West Omo, Konso, and Dawuro zones; within all Sidama Region zones; in the Southern Ethiopia Region the Walayita zone in many localities will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. Additionally, in the northern and eastern Shoa, northern west Tigray, northern and southern Gondar, western and eastern Gojjam, and northern and southern Wallo zones, heavy rainfall exceeding 30 mm is expected within 24 hours. On the other hand, in Semera, Elidar, Gambela, Fugnedo, Abobo, Melaka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Diredawa, Aisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Kebridahar, Gode, Chifra, and Metahara, high temperatures ranging from 35 to 40 degrees Celsius are anticipated.