Daily Weather Report 26 July 24

Weather Summary for previous day

July 23, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በሲዳማ ክልል ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳውሮ፣ ወላይታ፣ ቡርጂ፣ ሀዋሳ፣ መተከል፣ ማጃንግ፣ አኝዋክ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ፣ አውሲ፣ ፋንቲ፣ ሰሜን ምዕራብ እና ማዕከላዊ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በኮምቦልቻ 30.1፣ በዋራ ኢሉ 36.0፣ በጉንዶ መስቀል 35.6፣ በቢሾፍቱ 33.2፣ በጪራ 35.0፣ በኦቦ መርጋ 32.5፣ በደንጎላት 32.1፣ በፅጌሬዳ 31.3፣ አትናጎ 37.7 እና በጉጉፍቱ 36.8 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ ቀብሪደሃር፣ ጎዴ፣ ቡኢ፣ ፉኝዶ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.2-45.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

During yesterday, in the western, northern, northwestern, northeastern, central, and southern parts of our country cloudy conditions. Correlated with this feature, in Sidama region zone; Addis Ababa; Dire Dawa; Jimma,Ilubabor,Bunno Bedele,Horogudru,East and West Wellega,North, East,south west and West Shewa,West and East Hararge,Bale,West Arsi,Sheka,Bench Shako,West Omo,Dawuro,Walaita,Burji,Hawasa,Matakkal,Majang,Anuak,North,South and Centeral Gondar, Awi zone,Waghemra,North and South Wallo,West and East Gojjam,special zones of the Oromia Ethnic, the North Shoa, Awusi,Fanti,Soth west and Centeral the central Tigray zones, rainfall of light to moderate intensity was recorded. Specifically, in Kombolcha 30.1, in Wara Ilu 36.0, in Gundo Meskel 35.6, in Bishoftu 33.2, in Chira 35.0, in Obo Merga 32.5, in Dengolat 32.1, in Tsigereda 31.3, in Antago 37.7, and in Guguftu 36.8, with morning-to-afternoon rainfalls of heavy intensity recorded in some places. In other areas, such as Semera, Elidar, Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Kebridahar, Gode, Boji, Fungi Do and Metahara, the highest temperatures reached between 35.2–45.8°C.

Weather Forecast for next day

July 25, 2026

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ይበልጥ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ እና ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሰሜን ሸዋ፣ ጅማ፣ ሰሜን ምዕራብ ትግራይ፣ ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ጉራጌ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀድያ እና ደቡብ ወሎ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር፣ ጎዴ፣ ጭፍራ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

On the next day, rain with suitable atmospheric conditions for winter precipitation will continue more intensively across the northern, western, northwestern, northern eastern, eastern, southern western and central parts of our country. In addition, in connection with this, rain is expected in the following areas: the Oromia region’s zones of Jimma, Ilubabor, Bono, Horogudru, Qellem, East and West Wellega, North Wellega, Arsi and West Arsi, West and East Hararghe, Bale and East Bale, Gojjam; the Addis Ababa and Dire Dawa areas; the Amhara region’s western, northern, central and southern zones; the Afar region’s Awsi, Kilbeti, Gabi, Harari and Fanti zones; the Somali region’s Sitti zone; From central Ethiopia region’s Gurage, East Gurage,Mareko special zones,Silt’e,Yem special zone,Halaba,Hadiya zones, Kembata and Tembaro zones; From South West Ethiopia region’s Sheka, Bench Shako,Keffa,Konta and Dawuro zones; From South Ethiopia region’s Walayita zone in many localities, will receive rainfall ranging from light to moderate (1–29 mm) in those areas. In addition, in the northern Shoa, Jimma, the northern western Tigray, the Central Gondar, the western and eastern Gojjam,Gurage,Yem special zone, Hadiya, and the southern Wallo zones, will receive heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is reported. Similarly, in Semera, Elidar, Gambela, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Diredawa, Aisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Kebridahar, Kobo, Chifra, and Matahera, high temperatures ranging from 35 to 40 degrees Celsius are observed.