Daily Weather Report 26 July 21
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ዳውሮ፣ ጉራጌ፣ ማጃንግ፣ አኝዋክ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ዋግኸምራ፣ አዊ ዞን፣ ምስራቅ ትግራይ እና ደቡብ ወሎ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በነቀምቴ 50.7 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ ጋምቤላ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ኑራኤራ፣ ድሬዳዋ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ መሆኒ፣ ቀብሪደሃር፣ ጎዴ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.2-44.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were cloudy skies over parts of our country in the west, north, northwest, northeast, central and southwest. At the same time, Addis Ababa, Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, East Wollega, North, East, Southwest and West Shewa, Arsi and West Arsi, Assosa, Metekel, Wolayita, Gamo, West Arsi Omo, South Omo, Dawuro, Gurage, Majang, Agnuak, North, South and Central Gondar, West and East Gojjam, Wag Hemra, Awi Zone, East Tigray and South Wollo zones received light to moderate rainfall; in Nekemte a heavy rainfall of 50.7 mm was recorded. Elsewhere, in Semera, Elidar, Fugnedo, Gambella, Melka Jebdu, Nura Era, Dire Dawa, Dallifage, Awash Arba, Mehoni, Kebridahar, Gode and Metahara, daytime maximum temperatures ranged from 35.2 to 44.8°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ከፋ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጌዴኦ ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ማዕከላዊ ትግራይ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም እና መተከል ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር፣ ጎዴ፣ ጭፍራ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, weather conditions favorable for winter rain will continue over the northern, western, northwestern, northeaster, eastern, southwestern and central parts of the country. In connection with this, rain is expected in many areas of Oromia Region Jima, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shewa, Arsi and West Arsi, Bale, Guji and West Guji zones as well as in Addis Ababa and Dire Dawa. From Amhara Region: West, North, South and Central Gondar, Awi Zone, Wag Hemra, North and South Wollo, West and East Gojjam, and North Shewa zones. From Tigray Region: West, Northwest, East, South, Central and Southeast zones. From Gambela Region: Agnuak, Itang, Nuer and Majang zones. From Benishangul-Gumuz: Assosa, Metekel, Kamashi and Mao-Komo zones. From Afar Region: Awsi, Kilbati, Gabi, Hari and Fanti zones. From Somali Region: Siti Zone. From Central Ethiopia Region: Gurage, East Gurage, Mareko Special Zone, Silte, the special M/Zone, Halaba and Tambaro zones. From Southwest Ethiopia Region: Sheka, Bench Sheko and Kaffa zones. All zones of Sidama Region. From Southern Ethiopia Region: the Gedeo Zone. Many of these areas will receive light to moderate rainfall (1–29 mm). Additionally, in North and West Shewa, Central Tigray, West and East Gojjam and Metekel zones, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is expected. Meanwhile, high daytime temperatures between 35 and 40 degrees Celsius will be recorded in Semera, Elidar, Gambela, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhanssa, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Kebridahar, Gode, Chifra and Metehara.