Daily Weather Report 26 July 20

Weather Summary for previous day

July 19, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኸምራ፣ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣አዲስ አበባ፤ ሀዋሳ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ደቡብ ኦሞ፣ወላይታአሶሳ፣ፋፈን እና አኙዋክ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን ፉኙዶ 48.0፣ቦሬ 36.6፣ ባሌ ሮቤ 30.4 እና ኦሞ ናዳ 31.2 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመልካ ጀብዱ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ቀብሪደሃር፣ ጎዴ፣ ደጀን፣ ኑራ ኤራ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.6-39.5°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the western, northern, northwestern, northeastern, eastern, central, and southwestern parts of the country experienced cloud cover. In connection with this, light to moderate rainfall was recorded in North, West, South, and Central Gondar, West and East Gojjam, North and South Wollo, Wag Hemra, Jimma, Illubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, East and West Wollega, North, Southwest, East, and West Shewa, West and East Hararghe, Arsi and West Arsi, Bale and East Bale, Addis Ababa, Hawassa, West Omo, Sheka, Bench Sheko, South Omo, Wolaita, Asosa, Fafan, and Anuak zones. Additionally, heavy rainfall was recorded at Fugnido 48.0, Bore 36.6, Bale Robe 30.4, and Omo Nada 31.2 mm. On the other hand, the maximum daily temperature in Melka Jebdu, Dire Dawa, Aisha, Metema, Kebridahar, Gode, Dejen, Nura Era, and Metehara was recorded between 35.6-39.5°C.

Weather Forecast for next day

July 21, 2026

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ይበልጥ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ኮንታ፣ ከፋ እና ዳውሮ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ ማዕከላዊ ጎንደር፣ ዋግኸምራ፣ አሶሳ እና መተከል ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር፣ ጎዴ፣ ጭፍራ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, weather systems conducive to kiremt rain formation will continue to strengthen further over the northern, western, northwestern, northeastern, southwestern, and central parts of the country. In connection with this, most places in the Jimma, Illubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, East and West Wollega, North, East, Southwest, and West Shewa, Arsi and West Arsi, Bale, Guji, and West Guji zones of the Oromia Region; Addis Ababa; West, North, South, and Central Gondar, Awi zone, Wag Hemra, North and South Wollo, West and East Gojjam, and North Shewa zones of the Amhara Region; West, Northwest, East, South, Central, and Southeast zones of the Tigray Region; Anguak, Itang, Nuer, and Majang zones of the Gambella Region; Asosa, Metekel, Kamashi, and Mao Komo zones of the Benishangul-Gumuz Region; Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, Yem special zone, Halaba, Hadiya, Kembata, and Tembaro zones of the Central Ethiopia Region; Sheka, Bench Sheko, West Omo, Konta, Keffa, and Dawro zones of the Southwest Ethiopia Region; all zones of the Sidama Region; and Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, and Gedeo zones of the South Ethiopia Region will receive light to moderate rainfall ranging from 1 to 29 mm. Additionally, heavy rainfall of over 30 mm within 24 hours is expected in East Wollega, Horo Guduru, West Shewa, Central Gondar, Wag Hemra, Asosa, and Metekel zones. On the other hand, the maximum daily temperature will be recorded between 35-40°C in Semera, Elidar, Gambella, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhanssa, Mehoni, Dire Dawa, Aisha, Metema, Dalifage, Awash Arba, Kebridahar, Gode, Chifra, and Metehara.