Daily Weather Report 26 July 18

Weather Summary for previous day

July 17, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኸምራ፣ አዲስ አበባ፤ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ ሀዋሳ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ከፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጎፋ፣ ወላይታ እና ምዕራብ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በሾላ ገበያ 50.7፣ደብረ ብርሃን 32.7፣መሀል ሜዳ 47.6 ፣ወረኢሉ 47.0 ኢና ኮምቦልቻ 35.8 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል ድሬዳዋ፣ ፉኝዶ፣ ጎዴ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.2-37.8.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover over the western, northern, northwestern, northeastern, eastern, central, and southwestern areas of our country. In connection with this, North and Central Gondar, East Gojjam, North and South Wollo, Wag Hemra, Addis Ababa; Jimma, Illubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, East and West Welega, North, Southwest, and West Shewa, West Hararghe, Hawassa, West Omo, Sheka, Bench Sheko, Keffa, South Omo, Gofa, Wolaita, and West zones received light to moderate amounts of rainfall, while heavy amounts of rainfall were recorded in Shola Gebeya 50.7, Debre Berhan 32.7, Mehal Meda 47.6, Were Ilu 47.0, and Kombolcha 35.8 mm. On the other hand, Dire Dawa, Fugnido, Gode, and Metehara recorded daily maximum temperatures ranging from 35.2–37.8°C.

Weather Forecast for next day

July 19, 2026

በነገው ዕለት በምዕራብ አጋማሽ፣ በመካከለኛው፣በሰሜን እንዲሁም ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋንና ለዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የአየር ሁኔታ መረጃዎች ያመላክታሉ:: ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ፣ ማኦ ኮሞ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቂልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ እና ጋሞ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች በመነሳት በደቡብ ጎንደር፣ ዋግኸምራ፣ ጅማ፣ኢሉባቦር፣ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅና ቄለም ወለጋ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ ሸካ፣ ከፋ እና ጉራጌ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር፣ ጎዴ፣ ጭፍራ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

The rain producing weather systems are anticipated to continue in strengthen manner across the western half, central, northern, and eastern parts of the country and the aforementioned areas will have better cloud coverage. Hence, light to moderate rainfall (1–29 mm) is expected over many areas of the Central, Northwest, Southeast, South, and East zones of Tigray Region; North, West, South and Central Gondar, West and East Gojjam, Awi, North and South Wollo, Oromo special zone, North Shoa, and Wag Hemra zones of the Amhara region; Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, East, West, Kellem and Horo Guduru Wollega, West, Southwest, East and North Shoa, Arsi and West Arsi, West and East Hararghe, Bale, Guji and West Guji zones of the Oromia region; Addis Ababa; Harari; Dire Dawa; Assosa, Kamashi, Mao-komo, and Metekel zones of the Benishangul-Gumuz region; Majang, Nuwer, and Itang zones of Gambella region; Sheka, Bench Sheko, Kaffa, Konta, Dawuro, and West Omo zones of South West Ethiopia region; Gurage, Silte, Yem special zone, Halaba, Hadiya, Kembata, and Tembaro zones of Central Ethiopia region; all zones of Sidama region; Awusi, Kilbeti, Gabi, Hari, and Fanti zones of Afar region; Siti and Fafan zones of Somali region; and Wolaita and Gamo zones of South Ethiopia region. Moreover heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is expected over South Gondar, Wag Hemra, Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, East and Kellem Wollega, West Shoa, Sheka, Kaffa, and Gurage zones from intensified weather systems. On the other hand, daytime maximum temperatures of 35 to 40°C will be recorded in Semera, Elidar, Gambella, Fugnedo, Abobo, Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Kebri Dehar, Gode, Chifra, and Metehara stations.