Daily Weather Report 26 July 17

Weather Summary for previous day

July 16, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ፋፈን፣ ሀዋሳ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ወላይታ፣ ዳውሮ፣ አኝዋክ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜን ሸዋ፣ አዊ ዞን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ አዲስ አበባ 33.2፤ በደባርቅ 31.0፣ በጉንዶ መስቀል 31.7፣ በሆዕሳና 41.1 እና በጎብዬሬ 35.6ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ዳሊፋጌ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ድሬዳዋ፣ አዋሽ አርባ፣ ጨፋ፣ ባቲ፣ ዴጋን፣ ጎዴ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-40.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday there were cloudy patches over the western, northern, northwestern, northeastern, eastern, central and southwestern parts of our country. In addition, Addis Ababa; Jimma; Ilubabor; Buno Bedelle; Horo Guduru; East and West Wollega; North, Southwest and West Shewa; West Arsi; Bale; West and West Hararghe; West Guji; Fafan; Hawassa; Assosa; Metekel; West and South Omo; Gamo; Gofa; Walayita; Dawuro; Agnuak; western, northern, southern and central Gondar; West and East Gojjam; Wag Hemra; North Shewa; Awi Zone; and South Wollo zones received light to moderate rainfall. Heavy rainfall was recorded in Addis Ababa 33.2 mm, Debark 31.0 mm, Gundo Meskel 31.7 mm, Hosana 41.1 mm and Gobyere 35.6 mm. On the other hand, Metema; Dallifage; Melka Jebdu; Dire Dawa; Awash Arba; Chefa; Bati; Degan; Gode; and Metehara recorded daytime high temperatures ranging from 35.0 to 40.0°C.

Weather Forecast for next day

July 18, 2026

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች ፤ ከአፋር ክልል የአውሲ ዞን፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ እና ዳውሮ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ እና ጌዲኦ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በምዕራብ አርሲ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ሰሜን ጎንደር እና ማዕከላዊ ትግራይ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር፣ ጎዴ፣ ጭፍራ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Suitable weather systems for producing winter rain will continue tomorrow over northern, western, northwestern, northeastern, eastern, and southwestern areas and central parts of the country. In connection with this, parts of Oromia (Jimma, Iluababora, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shewa, Arsi and West Arsi, Bale, West and West Hararghe, Guji and West Guji zones; Addis Ababa; Dire Dawa; from Amhara region West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Wag Hemra, North and South Wollo, West and East Gojjam, Oromia Special Zone and North Shewa zones; from Tigray region West, Northwest, Northeast, South, Central and Southeast zones); from Afar region Awusi zone); from Gambela region Agnuak, Itang, Nuer and Majang zones); from Benishangul-Gumuz Assosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones; from Central Ethiopia region Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silte, Yem special zone, Halaba, Hadiya, Kambata and Tembaro zones); from South West Ethiopia region Sheka, Keffa and Dawuro zones; all zones of Sidama region; and from Southern Ethiopia region Walayita and Gedeo zones will receive light to moderate rainfall ranging from 1 to 29 mm in many places. In addition, western Arsi, Horo Guduru, East Wollega, southern, central and northern Gondar and central Tigray zones are expected to see heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours. Elsewhere, Semera, Elidar, Gambela, Fugnedo, Abobo, Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Aisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Kebridahar, Gode, Chifra and Metehara will record high daytime temperatures between 35 and 40 degrees Celsius.