Daily Weather Report 26 July 16

Weather Summary for previous day

July 15, 2026

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ፣ ማጃንግ፣ አኝዋክ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ አዊ ዞን፣ ምስራቅና ማዕከላዊ ትግራይ እና ደቡብ ወሎ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በማንደር11 46.5፣ በሻምቡ 40.8፣ በጅማ 38.6 እና በአሺ 32.4 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጭፍራ፣ ፉኝዶ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ዴጋን፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ አዋሽ አርባ፣ አቦምሳ፣ ሚኤሶ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ጎዴ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-44.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday there were cloudy patches over western, northern, northwestern, northeastern, eastern, central and southwest parts of our country. In connection with this, heavy rainfall was recorded in Addis Ababa, Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shewa, West Arsi, West and West Hararghe, Assosa, Metekel, Sheka, Bench Sheko, Dawuro, Majang, Agnuak, North, South and Central Gondar, West and East Gojam, North Shewa, Awi Zone, East and Central Tigray and South Wollo zones, ranging from light to moderate intensity; while very heavy rainfall amounts were measured at Villege11 46.5 mm, Shambu 40.8 mm, Jimma 38.6 mm and Ashi 32.4 mm. Elsewhere, unusually high daytime temperatures ranging from 35.0–44.0°C were recorded at Semera, Elidar, Cheffa, Fugnido, Melka Jebdu, Degan, Dire Dawa, Aisha, Awash Arba, Abomsa, Meiso, Mayhansa, Mehoni, Gode and Metehara.

Weather Forecast for next day

July 17, 2026

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረሪ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች ፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች፣ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ እና ዳውሮ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ እና ጌዲኦ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ደቡብና ሰሜን ጎንደር፣ ማዕከላዊ ትግራይ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ጉራጌ እና ስልጤ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር፣ ጎዴ፣ ጭፍራ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, weather conditions favorable for winter rain will persist across northern, western, northwest, northeast, southwest, and central parts of the country. In addition, the following zones and areas are expected to receive light to moderate rainfall (1–29 mm) in many places: from Oromia region Jimma, Iluababora, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shewa, Arsi and West Arsi, Bale, West and West Hararghe, Guji and West Guji zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harari; from Amhara region West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Wag Hemra, North and South Wollo, West and East Gojjam, Oromia Special Zone and North Shewa zones; from Tigray region West, Northwest, East, South, Central and Southeast zones; from Afar region Awusi, Kilbati, Gabi, Hari and Fanti zones; from Somali region Siti and Fafan zones; from Gambela region Agnuak, Itang, Nuer and Majang zones; from Benishangul Gumuz Assosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo zones; from Central Ethiopia Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silt’e, Mu special zone, Halaba, Hadiya, Kambata and Tembaro zones; from South West Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Kaffa and Dawuro zones; throughout all zones of Sidama region; and from Southern Ethiopia region Wolayita and Gedeo zones. Furthermore, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is expected over Arsi and West Arsi, Horo Guduru, Southwest Shewa, South and North Gondar, Central Tigray, East Gurage, Gurage and Silt’e zones. On the other hand, daytime maximum temperatures between 35 and 40 degrees Celsius will be recorded in places such as Semera, Elidar, Gambela, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Kebridahar, Gode, Chifra and Metehara.