Daily Weather Report 26 July 15
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ አኝዋክ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን እና ማዕከላዊ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ዴጋን፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር፣ ጎዴ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.3-45.8°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were cloudy patches over the western, northern, northwest, northeast, eastern, central and southwest parts of the country. In addition, rainfall of light to moderate intensity was recorded in Addis Ababa; Jimma; Illubabor; Buno Bedelle; Horo Guduru; East and West Wollega; West Shewa; West Hararghe; Asosa; Metekel; Agnuak; northern, southern and central Gondar; South Wollo; western and eastern Gojjam; Awi Zone; and central Tigray zones. On the other hand, daytime maximum temperatures between 35.3°C and 45.8°C were recorded in Semera; Elidar; Fugnido; Melka Jebdu; Dega; Dire Dawa; Aysha; Awash Arba; Qabri Dehar; Gode; and Metehara.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረሪ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች ፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች፣ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ እና ዳውሮ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ እና ጌዲኦ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ደቡብ ጎንደር፣ ደቡብ ምስራቅ ትግራይ፣ ጉራጌ እና ስልጤ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር፣ ጎዴ፣ ጭፍራ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, weather conditions favorable for winter rain will continue over northern, western, northwestern, northeastern, southwestern and central parts of the country. In addition, the following zones are expected to receive light to moderate rain (1–29 mm) in many places: from Oromia region Jimma, Ilubabora, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, North, East, South West and West Shewa, Arsi and West Arsi, Bale, West and West Hararghe, Guji and West Guji zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harari; from Amhara region West, North, South and Central Gondar, Awi zone, Wag Hemra, North and South Wollo, West and East Gojjam, the Oromia Special Zone, and North Shewa zones; from Tigray region West, Northwest, Northeast, South, Central and Southeast zones; from Afar region Awsi, Kilbati, Gabi, Hari and Fanti zones; from Somali region Sitti and Fafan zones; from Gambela region Agnuak, Itang, Nuer and Majang zones; from Benishangul-Gumuz Assosa, Metekel, Kamashi and Mao-Komo zones; from Central Ethiopia region Gurage, East Gurage, Mareko special zone, Silt'e, Halaba,Hadiya,Kambata and Tambaro zones; from Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Keffa and Dawuro zones; all zones of Sidama region; and from Southern Ethiopia region Wolayita and Gedeo zones. Additionally, heavy rain exceeding 30 mm in 24 hours is expected over Jimma, Arsi and West Arsi, South Gondar, Southeast Tigray, Gurage and Silt'e zones. Elsewhere, very high daytime temperatures of 35–40 degrees Celsius will be recorded in Semera, Elidar, Gambela, Funyido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhanssa, Mehoni, Dire Dawa, Aysha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Kebridahar, Gode, Kelafo, Chifra and Metehara.