Daily Weather Report 26 July 14
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛዉ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሀዋሳ፤ ሐረር፤ በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አሶሳ፣ መተከል፣ አኝዋክ፣ ማጃንግ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በፉኝዶ 36.6፣በመንደር11 34.2፣ በአሶሳ 39.5፣ በጌምቤ 47.5 እና በመካነ ኢየሱስ 39.4 ሚሜ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ፉኝዶ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጨፋ፣ ጎዴ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.2-44.0°C ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were cloudy conditions over western, northern, northwestern, northeast, eastern, central, southern and southwest parts of the country. In connection with this, Addis Ababa, Dire Dawa, Hawassa, Harar, Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shewa, West and West Hararghe, Asosa, Metekel, Agnuak, Majang, western, northern, southern and central Gondar, West and East Gojjam, Awi zone, northwest and central Tigray zones received light to moderate rainfall. Heavy rainfall amounts were recorded at Funyido 36.6 mm, Mender 11 34.2 mm, Asosa 39.5 mm, Gembel 47.5 mm and Mekane Iyesus 39.4 mm. On the other hand, high daytime temperatures ranging from 35.2–44.0°C were recorded at Semera, Elidar, Funyido, Melka Jebdu, Mayhanssa, Dire Dawa, Aisha, Metema, Dallifage, Awash Arba, Chefa, Gode and Metehara.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ይበልጥ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች ፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤኒሸንጉል ጉሙዝ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ እና ዳውሮ ዞኖች፤ በሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ እና ጌዲኦ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ትግራይ፣ ኢሉባቦር እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ኤሊዳር፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ በመልካ ጀብዱ፣ ማይሀንሳ፣ መሆኒ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ መተማ፣ ዳሊፋጌ፣ አዋሽ አርባ፣ ቀብሪደሃር፣ ጎዴ፣ ጭፍራ እና መተሐራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, weather conditions favorable for winter rain will be stronger and more persistent over northern, western, northwestern, northeastern, southwestern and central parts of the country. Accordingly, rainfall is expected in the Oromia regions of Jimma, Iluababora, Buno Bedelle, Horo Guduru, Kellem, East and West Wollega, North, East, Southwest and West Shewa, Arsi and West Arsi, Bale, Guji and West Guji zones; in Addis Ababa; in Amhara regions of West, North, South and Central Gondar, Awi Zone, Wag Hemra, North and South Wollo, West and East Gojjam, the Oromia Special Zone and North Shewa zones; in Tigray regions of West, Northwest, East, South, Central and Southeastern zones; in Afar zones of Awsi, Kilbati, Gabi, Hari and Fanti; in Gambela zones of Agnuak, Itang, Nuer and Majang; in Benishangul Gumuz zones of Assosa, Metekel, Kamashi and Mao Komo; in Central Ethiopia regions of Gurage, East Gurage, Mareqo special zone, Silte, the Me zone, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro zones; in Southwest Ethiopia region zones of Sheka, Bench Sheko, Kafa and Dawuro; in all zones of Sidama region; and in Wolayita and Gedeo zones of Southern Ethiopia where rainfall amounts will range from light to moderate, about 1–29 mm in many places. Additionally, in southern Gondar, northwest and central Tigray, Iluababora and West Shewa zones, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is expected. Elsewhere, daytime maximum temperatures between about 35 and 40 degrees Celsius are expected in Semera, Elidar, Gambela, Fugnido, Abobo, Melka Jebdu, Mayhansa, Mehoni, Dire Dawa, Ayshe, Metema, Dallifage, Awash Arba, Kebridahar, Gode, Chifra and Metehara.